Web Analytics Made Easy - Statcounter

See also ebooksgratis.com: no banners, no cookies, totally FREE.

CLASSICISTRANIERI HOME PAGE - YOUTUBE CHANNEL
Privacy Policy Cookie Policy Terms and Conditions
Wikipedia - እሪያ

እሪያ

ከWikipedia

እሪያ
እሪያ

እሪያ የዐሣማ ዓይነት የሆነ አውሬ ነው። የሚገኝበት አገሮች በማዕከለኛ አውሮጳ፣ በሜዲቴራኔያን አካባቢ፣ በስሜን አፍሪቃ ተራሮችም፣ በእስያ እስከ ኢንዶኔዝያ ድረስ ያጠቅልላል። ዛሬ በኢትዮጵያ ባይገኝም እሪያ በአፍሪቃ ውስጥ የሚኖር የከርከሮ ዘመድ ነው።

እሪያዎሽ የሚገኙበት ሃገራት
እሪያዎሽ የሚገኙበት ሃገራት

እሪያዎች እስከ 200 ኪሎግራም ድረስ ክብደት ሊያድጉ እርዝመታቸውም እስከ 1.8 ሜትር ድረስ ሊሆኑ ይቻላል። አደጋ ቢደርስባቸው እጅግ ጥለኛዎች ሆነው በረጅም ጥርሳቸው ጉዳት ለማድረግ ችሎታ አላቸው። ነገር ግን ይህ እምባዛም ሲደረግ አብዛኛው ጊዜ አንስት እሪያ ግልገሎችዋን አስጠብቃ ለመከላከል ሲያስፈልጋት ብቻ ይሆናል።

ከእሪያ እና ከዐሣማ መካከል ያለው ልዩነት እሪያ በጫካ ውስጥ የሚገኝ አውሬ ሲሆን ዐሣማ ግን ሰው ልጅ ያለመደ ማለት ነው። ዐሳማዎችም አምልጠው ወደ ጫካ ሲመለሱ እንደገና አሪያዎች ቶሎ ይሆናሉ። የእሪያ ቆዳ ባቀመቀመ ጽጉር ይሸፈናል። አውራ እሪያ ባቻ እንደ ከርከሮ የረዠመ ጥርስ አለበት።

በጃፓን ያለ የእሪያ አደጋ ምልክት
በጃፓን ያለ የእሪያ አደጋ ምልክት

የእሪያ መንጋ ቁጥር በተለመደ 20 እንስሶች ያህል ሲሆን ከ50 በላይ ያሉበት ስብሰባ ታይቶ ያውቃል። በተለመደ አንድ መንጋ 2 ወይም ሦስት አንስቶችና ግልገሎቻቸው ብቻ ናቸው። አውራዎቹ በብዛት ለብቻቸው እንጂ ከመፀዉ መርቢያ ወራት በስተቀር በመንጋው ውስጥ አይገኙም። የሚወልዱበት ወራት ጸደይ ሲሆን በተለመደ አምስት ግልገሎች ይወለዳሉ። እስከ 13 ድረስ ግን ሲቀፈቀፉ ታውቋል።

በብዛት እርያዎች የሌሊት እንስሶች ናቸው። ከማታ እስከ ንጋቱ ድረስ መኖ አሰብስበው በሌሊትም በመዓልትም ያርፋሉ። ምክንያቱም የሚያድኑዋቸው በተለይ በቀን የሚሄዱ ነው። እርያዎች ያገኙትን ማንኛውንም ነገር ያሕል ለምሳሌ ለውዝ፣ እንጆሪ፣ የበሰበሰ ሥጋ፣ ስሮች፣ ቆሻሻ፣ ነፍሳት፣ እንሽላሊት የመሰሉትን ትንንሽ ፍጡሮችና የአጋዘን ወይም የበግ ግልገሎች ሳይቀር የሚበሉ።

ከጥንታዊ ሮማ በ3ኛው ምዕተ ዘመን የተቀረጸ የእሪያ ማደን ምስል
ከጥንታዊ ሮማ በ3ኛው ምዕተ ዘመን የተቀረጸ የእሪያ ማደን ምስል

በአንዳንድ አገር ባሕል ስጋቸው ስለሚበላ ብቻ ሳይሆን ደግሞ በነሱ ምክንያት በሰብል ወይም በእርሻ የሚደረገውን ጉዳት ለመቀነስ ነው የሚያደኑዋቸው።

በታሪካዊ ልማድ የእርያ ማደን በልዩ ጦር አይነት ይፈጸም ነበር። የተናደደው እሪያ የተወጋ ገላ በጦሩ በኩል በመግፋት አዳኙን እንዳያጠቃ በረጅም እጀታ ላይ ባሻገር የገጠመ አገዳ ክፍል ነበረበት። የአዳኞቹ ውሾች እንኳን የቆዳ ጥሩር ለብሰው ነበር።

በፋርስ የእርያ አዳኝ ሌላ ዘዴ ይጠቅሙ ነበር። ከሕንድ አገር ዝሆን አምጥተው እርያዎቹን አባርረው በረግረግ ውስጥ ይከቡዋቸው ነበር። ይህን የመሰለ ትርዒት በገደል ድንጋይ ጎን ላይ በፋርስ ተቀርጾ ይገኛል።

ግሪክና በአይርላንድ አፈታሪክ ስለ እርያ ማደን ያሉ ተረቶች አሉ። በኖርስ አረመኔ እምነት አማልክታቸው ለማዳ እሪያዎች ነበሯቸው። እንዲሁም በሕንድ እምነት የቪሽኑ ሦስተኛ ትንሳኤ እሪያ ነበር። በፋርስም ስለጉብዝናው ይከብር ነበር። ደግሞ እርያ ለእንግሊዝ ንጉስ 3 ሪቻርድ ምልክት ነበር። እሪያ የእሪያም ራስ በአውሮጳ የጋሻ ስእል ስርዐት (አርማ) ብዙ ጊዜ ይታያሉ።

ባንዳንድ አገር የእሪያ ጽጉር ባለፈው ዘመን ለጥርስ መፋቂያ ይጠቅም ነበር። ነገር ግን ይህ ለንጽሕና የተሻለው ነገር አልነበረም።

[ለማስተካከል] የውጭ መያያዣ


aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -