>


Web - Amazon

We provide Linux to the World


We support WINRAR [What is this] - [Download .exe file(s) for Windows]

CLASSICISTRANIERI HOME PAGE - YOUTUBE CHANNEL
SITEMAP
Audiobooks by Valerio Di Stefano: Single Download - Complete Download [TAR] [WIM] [ZIP] [RAR] - Alphabetical Download  [TAR] [WIM] [ZIP] [RAR] - Download Instructions

Make a donation: IBAN: IT36M0708677020000000008016 - BIC/SWIFT:  ICRAITRRU60 - VALERIO DI STEFANO or
Privacy Policy Cookie Policy Terms and Conditions
Wikipedia - ታሪካዊ አቆጣጠር በየክፍለዘመኑ

ታሪካዊ አቆጣጠር በየክፍለዘመኑ

ከWikipedia

ይዞታ

[ለማስተካከል] ከክርስቶስ ልደት በፊት

  • 2700 ገ. የጊዛ ታላቅ እስፊንክስግብጽ ተሠራ።
  • 2360 ገ. - የሱመር ከተማ ላጋሽ አለቃ ኡሩካጊና ያዋጀ ሕገ ፍትሕ በታሪካዊ መዝገብ እስከምናውቀው ድረስ መጀመርያ የሕገ መንግሥት ሰነድ ነው።
  • 2330 ገ. ኤላም በ1 ሳርጎን ወደ አካድ መንግሥት ተጨመረና አካድኛን ይፋዊ ቋንቋ አደረገበት።
  • 2250 ገ. - የአካድ ንጉሥ ናራም-ሲን ስሜን ሶርያን ወርሮ በአሞራውያን ላይ ዘመተባቸው።
  • 2240 ገ. - የአካድ መንግሥት ተሰብሮ ኤላማዊው አገረ ገዡ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ በአመጽ ተነሥቶ አገሩን ነጻ አወጣውና አካድኛን ተወ።
  • 2100 ገ. - የኡር ንጉሥ የኡር-ናሙ ሕገጋት ከተገኙት ሕገጋት ሁሉ ጥንታዊ ነው።
  • 2055-2047 ገ. - የኡር ንጉሥ አማር-ሲን ነገሠ።
  • 2030 ገ. - የኡር ንጉሥ ሹ-ሲን ሴት ልጁን ለአንሻን መስፍን በትዳር ሰጠ።
  • 2012 ገ. - በሺማሽኪ ንጉስ በኪንዳታ መሪነት ኤላማውያን ከሹሻን ሕዝብ ጋር ኡር ከተማን አጠፉና ንጉሣቸውን የሹ-ሲን ልጅ ኢቢ-ሲንን ማረኩት።
  • 1978 ገ. - የኤፓርቲ ሥርወ መንግሥት በኤላም ጀመረ።
  • 1900 ገ. - በል-ካፕ-ካፒ በአሦር ነገሠ።
  • 1850 ገ. - ከሹሻን ወደ ስሜን በሆነ ከተማ የነገሠ ኤላማዊ ንጉሥ ኩዱር-ማቡግ ልጁን ዋራድ-ሲን በላርሳ ዙፋን ላይ አስቀመጠ።
  • 1820 ገ. - አሞራዊው ንጉሥ ሻምሺ-አዳድ አገሩን ከነአሦር ከተማ አቀና።
  • 1800 ገ. - ቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት በዋዲ ኤል ሖል ግብጽ
  • 1770 ገ. - ሃሙራቢ ኤላማውያን አስወጥቶ የላርሳ ንጉሥ ሪም-ሲን ገለበጠውና ሜስጶጦምያን በሙሉ ገዛ።
  • 1603 ገ. - ኬጢያውያን ባቢሎንን አሸነፉ ካሳውያን በሜስጶጦምያ ተነሡ።
  • 1500 ገ. - ቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት በደብረ ሲና በኩል
  • 1500-1400 ገ. - የኪዳኑ ስርወ መንግሥት በኤላም
  • 1400-1210 ገ. - የኢጊሃልኪ ሥርወ መንግሥት በኤላም
  • 1370 ገ. ሚታኒ በኬጢያውያን ግፊት ሲወድቅ የአሦር ንጉስ አሹር-ኡባሊት ነጻነቱን አዋጀ።
  • 1330 ገ. - የካሳውያን ንጉስ 2 ኩሪጋልዙ ለጊዜው ኤላምን ወረረ።
  • 1290 - የአሦር ንጉስ 1 አዳድ-ኒራሪ የሚታኒን መንግሥት አሸነፈ።
  • 1240 ገ. - ካሳዊ ንጉስ 4 ካሽቲሊያሽ ከኤላም ጋር ሲዋግ አላከናወነም።
  • 1232 - የኤላም ንጉሥ ኪዲን-ሑትራን የካሳውያን ንጉሥ ኤንሊል-ናዲን-ሹሚ አሸነፈ። * 1230 - የካሳውያን ንጉስ አዳድ-ሹማ-ኢዲና በኤላም ላይ አሸነፈ።
  • 1210-1100 - የሹትሩክ ሥርወ መንግስት በኤላም
  • 1184 - የኤላም ንጉሥ ሹትሩክ-ናሑንተ ከካሳውያንን ጋር ሲዋጋ የሃሙራቢ ሕገጋት የተጻፈበትን ድንጋይ ከመማረኩ በላይ የማርዱክና የማኒሽቱሹ ጣኦታትና የናራም-ሲን ሐውልት ወደ ሱስን ማረከባቸው።
  • 1190 ገ. - የኬጢያውያን መንግሥት በሙሽኪ (ፍሩጋውያን) ግፊት ወደቀ።
  • 1166 - የኤላም ንጉሥ ሹትሩክ-ናሑንተ ካሳውያንን በፍጹም ድል አደረጋቸው።
  • 1140 - የአሦር ንጉስ 1 አሹር-ረሽ-ኢሺ በአሞራውያን አገር በባቢሎንን ንጉሥ 1 ናቡከደነጾር ላይ አሸነፈ።
  • 1130 - ሱስን ለባቢሎን ንጉሥ ለ1 ናቡከደነጾር ወደቀና የኤላም ንጉሥ ሑተሉሽ-ኢንሹሺናክ ወደ አንሻን ሸሸ።
  • 992-987 - የባቢሎን ንጉሥ ማር-ቢቲ-አፕላ-ኡሹር ነገሠ።
  • 920 - 2 አዳድ ኒራሪ ንጉሥ ሆኖ የአሦር ሃይል ታደሰ።
  • 890 - የአሦር ንጉስ አሹር-ናሲር-ፓል ነግሦ ያለ ምኅረት ጠረፎቹን ያስፋፋ ጀመር።
  • 865-831 - 3 ስልምናሶር በአሦር ነገሠ።
  • 831-819 - 5ኛ ሻምሺ-አዳድ በአሦር ነገሠ።
  • 818-790 - 3 አዳድ-ኒራሪ በአሦር ነገሠ።
  • 784 ገ. - አልያቴስ በልድያ ነገሠ።
  • 755 - አሦር በብሔራዊ ጦርነት ተይዞ ባቢሎን በንጉሱ ናቦፖላሣር መሪነት ነጻነቱን አዋጀ።
  • 754 - ፎሐ (ፑሉ) የሚባል አለቃ የአሦር መንግሥት ቀምቶ 3 ቴልጌልቴልፌልሶር ተብሎ ንጉስ ሆነ።
  • 751-725 - የኤላም ንጉሥ ሑምባኒጋሽ ነገሠ።
  • 748 - ቴልጌልቴልፌልሶር አርፋድን አጠፋ፤ ሐማትንም ያዘ።
  • 746 - ቴልጌልቴልፌልሶር ፊልሥጥኤምን ወርሮ የእስራኤልን ንጉስ ምናሔምን 1000 መክሊት ብር አስገበረ።
  • 740 - የእስራኤል ንጉስ ፋቁሔ ከሶርያ (አራም) ንጉስ ረአሶን ጋራ አደጋ በይሁዳ ላይ ሲጣሉ የይሁዳ ንጉሥ አካዝ የመቅደሱን ወርቅ ሰጥቶ ከቴልጌልቴልፌልሶር እርዳታ ጠየቀ።
  • 737 - ቴልጌልቴልፌልሶር ወደ ባቢሎን ወርዶ ንጉሱን ናቡ-ሙኪን-ዜሪ ማረከና እራሱ 'የባቢሎን ንጉስ ፑሉ' ተብሎ ዘውዱን ተጫነ።
  • 735 - 5 ስልምናሶር በአሦር ነገሠ።
  • 733 - የእስራኤል ንጉሥ ሆሴዕ ግብርን ባቋረጠ ጊዜ የግብጽ ጠባቂነት አገኘ። ስለዚህ ስልምናሶር ወርሮ ከሦስት አመት ትግል በኋላ ሰማርያን ያዘና የእስራኤልን ቅሬታ ወደ ሌላ አገሮች ሰደዳቸው።
  • 730 - ስልምናሶር ሰማርያን እየከበባት ድንገት ከሞተ በኋላ ሻለቃው 2 ሳርጎን ዙፋኑን ያዘ።
  • 718 እና 716 - የኤላም ንጉሥ 2ኛ ሹትሩክ-ናሑንተ በ2ኛ ሳርጎን ሠራዊት እጅ ድል ሆነ።
  • 708 - የሳርጎን ልጅ ሰናክሬም መሮዳክ-ባላዳንን ገልብጦ የራሱን ልጅ አሹር-ናዲን-ሹሚ በባቢሎን ዙፋን ላይ ንጉስ አደረገው።
  • 702 - ሹትሩክ-ናሑንተ በወንድሙ ሐሉሹ ተገድሎ ይህ ሐሉሹ አሹር-ናዲን-ሹሚንና ባቢሎንን ማረከው።
  • 697 - ሰናክሬም ባቢሎንን አጠፋው።
  • 695-660 - ጉጌስ በልድያ ነገሠ።
  • 661 - የአስራዶን ልጅ አስናፈር ሱስንን ድል አድርጎ ወረራት።
    • እስኩታውያን ሜዶንን ስለወረሩ የፋርስ ነገዶች ከዚያ ወደ አንሻን ፈልሰው ንጉሳቸው ተይስፐስ አንሻንን ማረከው።
  • 660 ገ. - መጀመርያ መሐለቅ በልድያ ተሠራ።
  • 660-629 - 2ኛ አርዲስ በልድያ ነገሠ።
  • 655 - የአሦር ንጉስ አስናፈር ሱሳን አጠፋ።
  • 648 - አስናፈር ኤላምን በሙሉ ሲያጠፋ እርሻቸውን በጨው ዘራ።
  • 629-618 ገ. - ሣድያቴስ በልድያ ነገሠ።
  • 628 - ድራኮ የሚባል ጸሃፊ የአቴና ከተማ ሕገጋት ጻፈ፤ ይህም ሕግ እጅግ ጨካኝ ሆኖ ይሙት በቃ ለማንኛውም ጥፋት ወሰነ።
  • 618-568 - 2ኛ አልያቴስ በልድያ ነገሠ።
  • 600 - የአቴና አለቃ ሶሎን አዲስ ሕገ መንግሥት ፈጠረ።
  • 595 - የባቢሎን ምርኮ - ይሁዳ በ2ኛ ናቡከደነጾር ተያዘ።
  • 593 - የሜዶን ንጉስ ኩዋክሻጥራ ልድያን ባጠቃ ግዜ፣ በአንድ ታላቅ ውግያ ግርዶሽ ድንገት መጥቶ ከዚያ ቀጥሎ በኪልቅያና በባቢሎን ነገሥታት አማካይነት ስምምነት ተደረገላቸውና ያንግዜ ሃሊስ ወንዝ የሜዶንና የልድያ ጠረፍ ሆነ።
  • 568-554 - ቅሮይሶስ በልድያ ነገሠ።
  • 554 - ቅሮይሶስ በፋርስ ንጉሥ በ2ኛ ቂሮስ እጅ ድል ስለ ሆኑ መንግሥቱ ወዲያው የፋርስ ክፍላገር ሆነ።
  • 546 - የፋርሶች አሐይመኒድ ነገሥታት ሱሳንን ያዙት።
  • 457 - ሮማውያን መጀመርያ «12ቱ ሰንተረዦች» የተባለውን ሕገ መንግሥት አወጡ።
  • 407 - ከአንድ ጨነፈር የተነሣ የሲቡላውያን መጻሕፍት ተማከሩና ሌክቲስቴርኒዩም የተባለው ሥነ ሥርዓት ለአማልክታቸው ጣኦት ተመሠረተ።
  • 375 - ለሲቡላውያን መጻሕፍት 10 ጠባቂዎች በሮማ ተሾሙ።
  • 350 ገ. - የግሪክ ፈላስፋ አሪስጣጣሊስ የሕገ መንግሥት ሀሣብ ለይቶ ዐወቀ።
  • 339 - የመቄዶን ንጉሥ ታላቁ እስክንድር ከፋርስ መንግሥት ጋር ሱሳን አሸነፈው።
  • 301 - ከሌላ ጨነፈር ቀጥሎ የሲቡላውያን መጻሕፍት ተማክረው መልሱ ጣኦቱን አይስኩላፒዩስ ወደ ሮማ ከኤፒዳውሮስ (በግሪክ) እንዲያመጡ ሆነ። ሆኖም የሮማ ሴናት በጦርነት ተይዞ ከአንድ ቀን ጸሎት በቀር ስለ አይስኩላፒዩስ ነገር ምንም አላደረገም።
  • 246 - 'የአበባ ጨዋታዎች' (Ludi Florales) በሲቡላውያን መጻሕፍት ምክር ተመሠረቱ።
  • 224 - የካርታጌና አለቃ ሃኒባል የሮማ ጭፍራ በካናይ ፍልሚያ ሲያጠፋ፥ መጻሕፍቱ ተማክረው እንደ ምክራቸው ሁለት ግሪኮችና ሁለት ጋውሎች በሮማ ገበያ በሕይወታቸው ተቀበሩ።
  • 214 - የሃን ሥርወ መንግሥት በቻይና ተመሠረተ።
  • 212 - በካርታጌና ጦርነት ጊዜ የሮማ አበጋዝ ስኪፒዮ አፍሪካኑስ ከሲቡላውያን መጻሕፍት ምክር የተነሣ የኩቤሌ ጣኦት ከፔሢኖስ አምጥቶ አምልኮቷን በሮማ አስገባ።
  • 141 - ሮማውያን ሰርዴስን ገብተው ልድያ ወዲያው በሮማ መንግሥት ውስጥ የእስያ ጠቅላይ ግዛት ክፍል ሆነ።
  • 96-86 - የሱላ መሪነት በሮማ
  • 91 - የዩፒተር መቅደስ በሮማ ተቃጥሎ የሲቡላውያን መጻሕፍት ጠፉ።
  • 84 - የሮማ ላይኛ ምክር ቤት (ሴናት) ተልእኮዎች የሲቡል ትንቢቶች እንዲያገኙ ላኩዋቸው።
  • 71 - 'በሮማ ሦስት ቆርኔሌዎሶች ሊገዙ ነው' ከሚል ከአንዱ ትንቢት የተነሣ ፑብሊዩስ ቆርኔሌዎስ ሌንቱሉስ ሱራ አንድ ሤራ አደረገ።
  • 63 - 12 ፕቶለሜዎስ ወደ ግብጽ ዙፋን እንዲመለሱ ሮማውያን ሥራዊቱን መላካቸውን ሲማከሩ፣ መብራቅ በድንገት የዩፒተር ጣኦት መታ። ስለዚህ የሲቡል መጻሕፍቶች ተማክረው 'ከግብጽ አንድ ንጉሥ መቸም እርዳታ ቢለምንሽ፣ ወዳጅነትሽ አይቀርለት እንጂ ጣርና አደጋ እንዳያገኙሽ ሥራዊት ከቶ አትሥጪው' የሚል ትንቢት በመገኘቱ ይህ ቃል የፕቶሎሜዎስን መመለስ በጣም አቆየ።
  • 52 - 'በጳርቴ ላይ ማሸነፍ የቻለው ንጉሥ ብቻ ይሆናል' ስለሚል ትንቢት ቄሣር በሮማ ሬፑብሊክ ላይ ንጉሥነትን በቶሎ እንደሚይዝ ያለ ጭምጭምታ ተፈጠረ።

[ለማስተካከል] ዓመተ ምህረት

  • 7 - በሮማ ንጉሠ ጢባርዮስ ቄሣር ዘመን የሮማ ቲቤር ወንዝ ሲጎርፍ አንዱ ቄስ የሲቢሊን መጻሕፍት እንዲማከሩ አስቦ ጢባርዮስ ምስጢራዊ ስለቆጠራቸው እምቢ አለ።
  • 17-212 - ሃን ስርወ መንግሥት በቻይና
  • 34 - 44 - ንግሥት ግርሳሞት ህንደኬ 7ኛ ዘመን በኢትዮጵያ
  • 71 - ደብረ ቬሱቪዩስ እሳተ ገሞራ በኢጣልያ 3 ከተሞችን አጠፋ።
  • 89 - ጋን ዪንግ በቻይና አበጋዝ ባን ቻው ወደ ሮማ ተላከ።

  • 108 - የሮማ ንጉስ ትራያኑስ ሱሳን ይዞ በአመጽ ምክንያት ቶሎ መመለስ ነበረበት። ይህም ሮማውያን ከሁሉ ወደ ምሥራቅ የደረሱበት ወቅት ነበረ።

  • 218-643 - የሳሳኒድ መንግሥት በፋርስ
  • 263 - ሮማውያን በፕላኬንቲያ ፍልሚያ[ በአላማኒ ጀርመኖች ከተሸነፉ በኋላ የሲቢሊን መጻሕፍት ተማከሩ።
  • 288 - በሮማ ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ ትዕዛዝ 'ልድያ' እንደገና የትንሽ ጠቅላይ ግዛት ስም ሆነ።

  • 303 - የሮማ ንጉሥ ጋሌሪዎስ አልጋ ላይ ወድቆ ትንሽ ሊያርፍ ሲል በመንግሥቱ ግዛት ውስጥ ላሉት ክርስቲያኖች ሁሉ ይቅርታ ሰጠ።
  • 304 - ከሚልቪያን ድልድይ ፍልሚያ አስቀድሞ የተቃዋሚ አለቆች ማክሰንቲያስና ቈስጠንጢኖስ ሲያዘጋጁ ማክሰንቲያስ የሲቢሊንን መጻሕፍት አማከሩና ቈስጠንጢኖስ እምነታቸውን ከአፖሎ ወደ ክርስቶስ አዛወሩ። በፊልሚያውም የማክሰንቲያስ ድል መሆኑ ስመ ጥሩ ድርጊት ነው።
  • 305 - ሁለት የጋርዮሽ ቄሣሮች 1ኛ ቈስጠንጢኖስ እና ሊቂኒዎስ የሚላኖ አዋጅን አወጡ። ይህ ህግ ለሰው ሁሉ የሃይማኖት ነጻነት በማረጋገጥ የክርስቲያኖች መሬት ያለ ገደብ እንዲመልስላቸው የሚያዝዝ ነበር።
  • 317 - ቆንስጣንጢኖስ የኒቂያ ጉባኤ ጠሩ።
  • 353 - የሮማ ንጉሥ ዩሊያኖስ ከሐዲ መንግሥቱን ለጥቂት ግዜ ወደ ድሮ አረመኔ እምነት መለሠው።
  • 355 - የሮማ ንጉሥ ዩሊያኖስ ከሐዲ በጳርቴ ላይ ዘመቻ ሊያደርግ ሲል መጻሕፍቱን አማከረ። ከሮማ የደረሰውም መልስ በዛኛው አመት ጠረፍ መሻገሩን በግልጽ ደገፈው።
  • 372 - የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በንጉሡ 1ኛ ቴዎዶስዮስ አዋጅ መሠረት የሮማ መንግስት ሃይማኖት በይፋ ተደረገ።
  • 397 - የአሪዮስ ክርስትና ትምህርት አራማጅ የሆነ ስቲሊኮ የሲቡላውያን መጻሕፍት በሮማ እንዳቃጠላቸው ይባላል።

  • 402 - ሮማ ከተማ በቪዚጎቶች ተዘረፈች።
  • 430 - መጽሐፈ ቴዎዶስዮስ ለምሥራቅ ሮማ ሕገ መንግሥት ሆነ።
  • 443 - የሮማ ንጉስ ያሰበሰበው የኬልቄዶን ጉባኤ ክርስቶስ ሁለት የተለያዩ ባሕርዮች እንደነበሩት አዋጀ።
  • 463 - የቪዚጎቶች አለቃ ዩሪክ ሕገ መንግሥት አወጣ።
  • 467 - የጀርመን አለቃ ኦረስቴስ የሮማ ነጉስን አባርሮ መጨረሻውን ንጉስ ሮሙሉስ አውግስጦስን ሾመ።
  • 492 ገ. - የቡርጎንዳውያን፣ የአላማናውያንና የፍራንኮች ሕገጋት ተጻፉ።
  • 498 - የቪዚጎቶች አለቃ 2ኛ አላሪክ መጽሐፈ ቴዎዶስዮስና አንዳንድ የተለያዩ የቀድሞ ሮማ ሐገጋት አከማችተው አዋጁአቸው።

  • 526 - መጽሐፈ ዩስጢኒያኖስ ባይዛንታይን ሕገ መንግሥት ወጣ።
  • 571 - በቻይና [[የመንግስት ሃይማኖት] የቡዳ ሃይማኖት ሆነ።
  • 596 - በጃፓን 17 አንቀጽ ያለ ሕገ መንግሥት በልዑል ሾታኩ ተጻፈ።

  • 602-633 - ቢዛንታይን ንጉሥ ሄራክሊዮስ ዘመን
  • 614 - ነቢዩ መሐመድ የመዲና ሕገ መንግሥት አወጣ።
  • 630 - የእስላም ሰራዊቶች ፋርስን በወረሩበት ጊዜ ሱሳ በጥፋት ላይ ተጣለ።
  • 635 - የሎምባርዶች ሕገጋት ተጻፉ።
  • 646 - የቪዚጎቶች አዳዲስ ሕገጋት ተጻፉ።

  • 722 - የአላማናውያን አዳዲስ ሕገጋት ተጻፉ።
  • 732 - የባይዛንታይን ንጉሥ ሌዎን ኢሳውራዊ «ኤክሎጋ» የተባለውን ሕገ መንግሥት አወጣ።
  • 742 - አባሲዶች ሥልጣን ይዘው ዋና ከተማቸውን ከደማስቆ ወደ ባግዳድ አዛወሩ።
  • 777 - የፍሪዝያውያን ሕገጋት ተጻፉ።

  • 800 ገ. - ስሜን እንግሊዝ በቫይኪንጎች ስለተወረረ በንጉስ አልፍሬድ ጊዜ የሴክሶች ቀበሌኛ ይፋዊ ሁኔታ አገኘ።
  • 870 - የባይዛንታይን ንጉሥ 1ኛ ባሲሌዎስ «ባሲሊካ» የተባለውን ሕገ መንግሥት አወጣ።

  • 936 - ታምራዊ መልክ ያለበት ስዕል ከኤደሣ ወደ ቊስጥንጥንያ ተዛወረ።

  • 1059 - ኖርማኖች እንግሊዝን ወረሩ።
  • 1088 - አንደኛው የመስቀል ጦርነት ተካሔደ።
  • 1092 - የእንግሊዝ ንጉስ 1 ሄንሪ የነጻነት ሥርአት የተባለውን ሰነድ አዋጀ።

  • 1110 - አዲስ የተቋቋመውን የእየሩሳሌም መንግስት ከእስላሞች ለመከላከልና ወደ ከአውሮፓ ወደ እየሩሳሌም የሚጎርፉትን ተሳላሚዎች ደህንነት ለመጠበቅ ቴምፕላርስ ተመሠረቱ።
  • 1184 - በመስቀል ጦርነት የእንግሊዝ ንጉስ 1 ሪቻርድ በሳላዲን ላይ በአርሱፍ ውግያ አሸነፈ።
  • 1196 - ፈረንጆች (መስቀለኞች) ቊስጥንጥንያን ዘረፉት።

  • 1207 - መኳንንቱ የእንግሊዝ ንጉሱን ዮሃንስ (ጆን) ማግና ካርታ ('ታላቅ ሥርዓት') የሚባለውን ሰነድ እንዲፈርሙት አስገደዱዋቸው።
  • 1210 - በወራሪ ሞንጎሎች እጅ ሱሳ በፍጹም ጠፋች።
  • 1212-1222 - አንድ የሳቅሰን አስተዳዳሪ አይከ ቮን ረፕጎቭ ሳቅሰንሽፒግል የተባለውን ሕገ ፍትኅ አቀነባበረ።
  • 1228 - ሱንዲያታ ከይታ ማሊ መንግሥትን ለማወሐድ የ'አፈ ቃል' ሕገ መንግሥት 'ኩሩካን ፉጋ' አወጡ።
  • 1240 ገ. - በግብጽ አገር ቅብጡ አቡል ፋዳዒል እብን አል-አሣል ፍትሐ ነገሥትአረብኛ ጻፉ።
  • 1250 - ሁላጉ ከሐን የተባለው የሞንጎሎች መሪ ባግዳድን ሲበዘብዝ የአባሲዶች መንግስት ፍጻሜ ለመሆን በቅቷል።
  • 1252 - እጣልያ የንጉስ ወገን በፓፓ ወገን በሞንታፔርቲ ድል አደረገ።
  • 1262 - ይኵኖ አምላክ ሥልጣን ጨበጠው የኢትዮጵያ መጀመሪያው የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት ዐፄ ሆኑ።

  • 1382 - የሰርዴስ ዙሪያ የኦቶማን ቱርክ መንግሥት ክፍል ሆነ።

  • 1400 - የቻይና ሰዎች ወርረው 'ዶንግ ዶ' (ሀኖይ)ን ይዘው ስሙን 'ዶንግ ጯን' አሉት።
  • 1420 - ዶንግ ጯን ወደ ቬትናም ሕዝብ ሲመለስ ስሙ 'ዶንግ ኪኝ' ሆነ።
  • 1431 - በአጼ ዘርዕ ያዕቆብ ዘመን አባ ጊዮርጊስ ከ1 ፈረንሳያዊ ጐባኝ ጋራ ስለ ሃይማኖት ስላነጋገሩ አንድ ተልእኮ ወደ ሮማ ተላከ።

[ለማስተካከል] 16ኛ ምዕተ ዓመት

  • 1500 - ኢትዮጵያ ከአዳል ጋር ስትታገል ማቴዎስ የተባለ አንድ አርሜናዊ ወደ ፖርቱጋል ተልኮ የፖርቱጋል ንጉስ እርዳታ ለመነ።
  • 1507 - የፖሎኝ ሠራዊት በኦርሻ ውግያ በሩስያ ላይ አሸነፈ።
    • - ሀቫና በእስፓንያውያን በኩባ ደቡብ ዳርቻ ተመሠርቶ ከተማው በዚህ ሥፍራ ግን አልተከናወነም።
  • 1511 - ሀቫና እንደገና በስሜን ዳርቻ ተመሠረተ።
  • 1512 - የፖርቱጋል ሚሲዮን በኢትዮጵያ ደረሰ።
  • 1514 - ቪክቶሪያ የምትባል መርከብ ወደ ስፓንያ በመመለሷ መጀመርያ ዓለምን የከበበችው መርከብ ሆነች።
  • 1525 - የእንግሊዝ ንጉሥ 8ኛ ሄንሪ የፕሮቴስታንት እምነት ስለ አጸደቀ፤ በፓፓ ፈንታ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ላይኛ መሪ ሆነ።
  • 1534 - ሳንቲያጎ ቺሌ በኗሪ አርበኞች ጠፋ።
  • 1547 - የአውሮፓ መንግሥታት የመሪዎቻቸውን ሃይማኖት ይከተሉ የሚለው የአውግስቡርግ ውል ጸደቀ።
  • 1557 - በዛሬው ዩናይትድ እስቴት ከሁሉ አስቀድሞ በአውሮጳውያን የተሰራ ከተማ ሰይንት ኦገስቲን፥ ፍሎሪዳ ተመሰረተ።
  • 1564 - ካቶሊኮች በፈረንሳይ ፕሮቴስታንቶች ላይ የበርተሎሜዎስ እልቂት ጀምረው መሪያቸውን ደኮልኒን ገደሉ።

[ለማስተካከል] 17ኛ ምዕተ ዓመት

  • 1601 - ጋሊሌኦ ስለመጀመርያ ቴሌስኮፕ ለቬኒስ አማካሪዎች መግለጫ ሰጠ።
  • 1602
    • መስከረም 4 ቀን - የስፓንያ ከተማ ቫሌንሲያ ሞሪስቾዎችን (አረብ ክርስቲያን) ሁሉ አባረራቸው።
    • መስከረም 5 ቀን - የእንግሊዝ መርከበኛ ሄንሪ ሀድሰን የሀድሰን ወንዝ (በዛሬው ኒው ዮርክ) አገኘው።
    • ኅዳር 23 ቀን - የስምምነት ውል ተፈራርመው፣ እስፓንያውያን በምሥራቅ ጃፓን ውስጥ አንድ ፋብሪካ ለመሥራት፣ የማዕድን ሠራተኞች ከ«አዲስ ስፓንያ» (ሜክሲኮ) ወደ ጃፓን ለማስገባት፣ የስፓንያ መርከቦች አስፈላጊነት እንደሆነባቸው ጃፓንን ለመጎብኘት ተፈቅደው፣ ደግሞ የጃፓን ተልእኮ ወደ እስፓንያ ቤተ መንግሥት እንዲጓዝ ተወሰነ።
    • ጥር 2 ቀን - ጋሊሌኦ በቴሌስኮፕ አዲስ ጨረቃዎች በጁፒተር ዙሪያ አገኘ።
    • መጋቢት 6 ቀን - የስዊድን ጭፍሮች መስኮብን ማረኩ።
    • ግንቦት 2 ቀን - ፍራንሷ ራቫያክ የፈረንሣይን ንጉሥ 4ኛ አንሪ ገደላቸው።
    • ሐምሌ 1 ቀን - ጆን ጋይ ከ39 እንግሊዛውያን ሰፈረኞች ጋራ ወደ ኒውፈንላንድ (የዛሬው ካናዳ) ከእንግሊዝ ወጣ።
    • ሐምሌ 29 ቀን - ሄንሪ ሀድሰን የሀድሰን ባህረሠላጤ (በዛሬው ካናዳ) አግኝቶ ወደ እስያ የሚወስድ ማለፊያ መሰለው።
  • 1617 - የኢትዮጵያ ንጉስ ሱስንዮስ ወደ ሮማ ፓፓ ተሰለሙ።
  • 1625 - ሱስንዮስ ዘውዳቸውን ለልጃቸው ለፋሲላድስ እንዲሰጡ ተደረጉ። ፋሲላድስ ወዲያው አገሩን ወደ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መለሱ።
  • 1626 - ፋሲላደስ ኢየሱሳውያን አገሩን ለቅቀው እንዲሄዱ አዘዙ።
  • 1641 - በኢጣልያ ካስትሮ የሚባል ከተማ በሮማ ፓፓ ላይ አመጽ አድርጎ፡ የፓፓ ሃያላት አጠፉት።
  • 1658 - በለንደን እንግሊዝ 10 ሺህ ሕንጻዎች ያጠፋ ታላቅ እሳት ጀመረ።
  • - በኢትዮጵያ ፋሲላድስ የኢየሱሳውያንን መጻሕፍት አስቃጠሉ።
  • 1676 - የአውሮፓ ሠራዊት በቪኤና ውግያ ቱርኮችን አሸነፉ።
  • 1690 - ፃር 1 ፕዮትር በሩሲያ የጺም ቀረጥ አስገበረ።

[ለማስተካከል] 18ኛ ምዕተ ዓመት

  • 1731 - በቻርልስተን፥ ሳውስ ካሮላይና አካባቢ ስቶኖ የባርዮች አመጽ ሆነ።
  • 1745 - ንጉሡ አላውንግፓያ የዳጎን አውራጃ አሸንፎ ስሙን ወደ ያንጎን ቀየረው።
  • 1768 -
    • ኅዳር 5 ቀን - የአሜሪካ አብዮታዊ አርበኞች ከፍልሚያ በኋላ ሞንትሬያልን ማረኩ።
    • ታኅሣሥ 23 ቀን - የእንግሊዝ ሠራዊት በኬበክ ከተማ አሜሪካውያንን አስመለሳቸው።
    • የካቲት 29 ቀን - በሞርዝ ጅረት ድልድይ ፍልሚያ ስሜን ካሮላይና አርበኞች አሸነፉ።
    • መጋቢት 10 ቀን - ከአሜሪካውያን መድፍ የተነሣ የእንግሊዝ ሠራዊት ከቦስቶን ይወጣል።
    • ሰኔ 3 ቀን - አሜሪካውያን በቷ-ሪቭዬር ፍልሚያ በኬበክ ድል ሆኑ።
    • ሰኔ 24 ቀን - ስፓንያውያን ሳን ፍራንሲስኮ ካሊፎርኒያ አቆሙ።
    • ሰኔ 29 ቀን - የአሜሪካ ነጻነት ዐዋጅ (ከእንግሊዝ አገር) በቶማስ ጄፈርሰን ተጽፎ በፊላዴልፊያ ታተመ።
    • ሐምሌ 4 ቀን - በኒው ዮርክ ከተማ ብዙ ሠልፈኞች ተናድደው የእንግሊዝ ንጉሥ 3ኛ ጆርጅን ሐውልት ያወድቃሉ።
    • ሐምሌ 7 ቀን - የእንግሊዝ ዠብደኛ ጄምስ ኩክ በሦስተኛው ጉዞ ወደ ሰላማዊ ውቅያኖስ ከእንግሊዝ ወጣ።
    • ነሐሴ 11 ቀን - የጀርመን ቅጥረኛ ወታደሮች የእንግሊዝ ሠራዊት ለመርዳት በኒው ዮርክ ደረሱ።
    • ነሐሴ 23 ቀን - የእንግሊዝ ሠራዊት በጆርጅ ዋሽንግተን ላይ በሎንግ አይላንድ ውጊያ አሸነፉ።
    • ጳጉሜ 3 ቀን - አንድ አውሎ ንፋስ ጉዋዶሎፕ ሲመታ ከ6000 ሰዎች በላይ ጠፉ።
  • 1773 -
  • 1775 - የአሜሪካ ነጻነት አብዮት ከእንግሊዝ በፓሪስ ውል ተጨረሰ።
  • 1784 - በፈረንሳይ አብዮት ከ200 በላይ ቄሳውንት ሰማዕትነት አገኙ።
  • 1785 - የፈረንሳይ አብዮታዊ አማካሪዎች "የማስፈራራት መንግስት" ዐዋጁ።
  • 1790 - የአንድ ሳምንት ባሕር ውግያ በእንግሊዝና በእስፓንያ መካከል ከቤሊዝ አጠገብ ጀመረ።
  • 1791 - ስልጣን ለመያዝ ናፖሌዎን ከግብፅ ወደ ፈረንሳይ ወጣ።
  • 1792 - ጌብሪየል ፕሮሰር የባርዮችን ብጥብጥ በሪችሞንድ ቪርጂንያ አሸፈተ።

[ለማስተካከል] 19ኛ ምዕተ ዓመት

  • 1804 - ናፖሊዎን በሩሲያ ላይ በቦሮዲኖ ውግያ ድል አደረገ።
  • 1805 -
    • መስከረም 5 - ናፖሊዎን እንዳይማርከው የሩሲያ ሰራዊት መስኮብን አቃጠለ።
    • ነሐሴ 22 - ናፖሌዎን በድረስደን ውጊያ ድል አደረገ።
    • ነሐሴ 25 - የናፖሌዎን ሠራዊት በኩልም ውጊያ ድል ሆነ።
    • ነሐሴ 25 - ክሪክ የተባለው የቀይ ኢንዲያን ጐሣ ወታደሮች በፎርት ሚምስ ምሽግ አላባማ ላይ እልቂት አደረጉ።
  • 1806 - የአሜሪካ መርከቦች በኤሪ ሐይቅ በእንግሊዝ አሸነፉ።
  • 1814 - ብራዚል ነጻነቱን ከፖርቱጋል አዋጀ።
  • 1822 -
  • 1825 - ባርነት በእንግሊዝ አገር ግዛቶች ሁሉ ባዋጅ ተከለከለ።
  • 1828 - ሳሙኤል ሁስተን የቴክሳስ ሬፑብሊክ መጀመርያ ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመረጠ።
  • - በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ።
  • 1830 - በሜሪላንድ ፍረድሪክ ዳግላስ መርከበኛ በማስመስል ከባርነት አመለጠ።
  • 1831
  • [[1844] - እንግሊዞች ያንጎን በጦርነት ሲይዙ ስሙን 'ራንጉን' አሉት።
  • 1850 - በሪችሞንድ ቪርጂኒያ 90 ጥቁሮች ትምህርት ስለተማሩ ታሰሩ።
  • 1854 - በአሜሪካ መነጣጠል ጦርነት ደቡብ ክፍላገሮች (ኮንፌዴራቶች) በ2ኛ መናሠሥ ውጊያ አሸነፉ።
  • 1862 -
  • 1865 - በአባታቸው በምፓንዴ መሞት ከትሿዮ የዙሉ ንጉስ ሆኑ።
  • 1869 - የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ጎልድ ኮስት (የአሁን ጋና) መቀመጫ ከኬፕ ኮስት ወደ አክራ ተዛወረ።
    • ጥቅምት 22 ቀን - ታላቅ አውሎ ንፋስ በሕንድ 200,000 ሰዎችን ገደለ።
    • ሚያዝያ 17 ቀን - ሩስያ በቱርክ ኦቶማን መንግሥት ላይ ጦርነት አዋጀ።
    • ሚያዝያ 29 ቀን - የላኮታ ኢንዲያን አለቃ ክሬዚ ሆርስ ለአሜሪካውያን ሠራዊት ዕጁን ሰጠ።
    • ግንቦት 14 ቀን - ሮማኒያ ነጻነቱን ከኦቶማን ቱርክ መንግሥት አዋጀ።
    • ጳጉሜ 1 ቀን - ክሬዚ ሆርስ በእስር ተገደለ።
  • 1871 - በደቡብ አፍሪቃ መጨረሻ የሆኑት የዙሉ ንጉሥ ከትሿዮ በእንግሊዞች ተማረከ።
  • 1875 - ክራካቶአ የተባለ እሳተ ገሞራ በእንዶኔዝያ ፈነዳ፤ 3600 ሰዎች ሞቱ።
  • 1878 - አዲስ አበባዳግማዊ ምኒልክ ተቆረቆረች።

ከምድር መንቀጥቀጥ በሳውስ ካሮላይና 100 ሰዎች ሞቱ።

    • ነሐሴ 30 ቀን - ከ30 አመት ትግል በኋላ፣ የአፓቺ አለቃ ጀሮኒሞ በአሪዞና እጅን ሰጠ።
  • 1881 - አይፈል ግንብ በፓሪስ ተሠራ።
  • 1883 -
  • መስከረም 3 ቀን - ሳልስበሪ፣ ሮዴዚያ ተመሰረተች።
  • ጥቅምት 9 ቀን - ዊንድሁክ ከተማ በጀርመኖች ተሠራ።
  • 1887 - የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ።
  • 1888 - ከዓለሙ ታሪክ አጭሩ ጦርነት - 38 ደቂቃ - የእንግሊዝ-ዛንዚባር ጦርነት
  • - በኢትዮጵያና በጣልያ የደረሰ የአድዋ ጦርነት።
  • 1890 -
    • የ ቦሊቪያ መንግሥት መቀመጫ ከሱክሬ ወደ ላፓዝ ተዛወረ።
    • 'ሎሬንሶ ማርኬስ' ከተማ (አሁን ማፑቶ) የፖርቱጋል ቅኝ አገር ሞዛምቢክ መቀመጫ ተደረገ።
    • መስከረም 1 - በላቲመር ፔንሲልቬኒያ ፖሊሶች 19 የማዕደን ሰራተኞች በእልቂት ገደሉ።
    • መስከረም 2 - የዳግማዊ ምኒልክ ሻለቆች የካፋን ንጉስ ጋኪ ሸሮቾ በማማረክ ያንን መንግስት ጨረሱ።
    • ታኅሣሥ 22 - እንግሊዞች በደቡብ አፍሪካ የዙሉ አገር ወደ ናታል አውራጃ አስቀጠሉ።
    • የካቲት 9 - የአሜሪካ መርከብ መይን በሃቫና ወደብ ኩባ ባልታወቀ ምክንያት ተፈነዳ።
    • ሚያዝያ 15 - የአሜሪካ መርከብ ሃይል የኩባ ወደቦችን ማገድ ጀመረ።
    • ሚያዝያ 18 - የአሜሪካ ምክር ቤት ከመይን መፈንዳት የተነሣ ጦርነት ከሚያዝያ 14 ጀምሮ እንደ ነበር በእስጳንያ ላይ አዋጀ።
    • ሚያዝያ 30 - በጣልያ አበጋዙ ባቫ-በካሪስ ብዙ መቶ ሰልፈኞች በመድፍ ገደላቸው።
    • ግንቦት 21 - ሴኮንዶ ፒያ የሚባል የፎቶ አንሺ የቶሪኖ ከፈን ፎቶ ሲታጠብ ኦሪጂናሉ ኔጋቲቭ መሆኑን አገኘ።
    • ሰኔ 6 - ፊሊፒንስ ደሴቶች ነጻነት ከስፓንያ አዋጀ።
    • ሐምሌ 1 - አሜሪካ የሃዋይኢ ደሴቶችን አስቀጠለ።
    • ሐምሌ 11 - አሜሪካውያን በስፓኒሾች ላይ በሳንቲያጎ ፍልሚያ ኩባ አሸነፉ።
    • ሐምሌ 19 - አሜሪካውያን ፕወርቶ ሪኮ ደሴት ወርረው ከስፓንያ ማረኩዋት።
    • ነሐሴ 7 - በኩባ በስፓንያውያንና በአሜሪካውያን መካከል ያለው መታገል ጨረሰ።
    • ነሐሴ 28 - በኦምዱርማን ውግያ ሱዳንእንግሊዝ ሠራዊት ድል በማድረግ በሙሉ ቅኝ አገር አደረጉት።
  • 1892 - ፖርቶ ኖቮፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ዳሆመይ (የዛሬ ቤኒን) መቀመጫ ተደረገ።
    • 'ፎርት-ላሚ' ከተማ (ዛሬ ንጃመናቻድ) በፈረንሳዊው አዛዥ ኤሚል ዣንቲ ተመሠረተ።
    • ነሐሴ 21 ቀን - የእንግሊዝ ሃያላት በአፍሪካነር (ቦር) ጦርነት (ደቡብ አፍሪቃ) በበርገንዳል ውጊያ አሸነፉ።
    • ጳጉሜ 3 ቀን - አንድ ታላቅ አውሎ ንፋስ በቴክሳስ 8000 ሰዎች አጠፋ።
  • 1893 -
    • መስከረም 3 ቀን - በፊሊፒንስ ጦርነት የፊሊፒንስ ተዋጊዎች በአሜሪካ ሠራዊት ላይ ድል አደረጉ።
    • ጳጉሜ 1 ቀን - ሌኦን ቾልጎሽ የተባለ ወንበዴ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት መኪንሊ ተኩሶ ገደለው።
  • 1894 - የአሜሪካ ፕሬዚዳንት መኪንሊ ተተኩሰው ሲሞቱ ቴዮዶር ሮዝቬልት ፕሬዚዳንት ሆኑ።
  • 1897 - ሉሳካ ለአለቃው ሉሳካ ተሰየመ።
    • ጣልያኖች ተከራይተው የነበረውን ሞቃዲሾን በዋጋ ገዙትና የጣልያ ሶማሊያ መቀመጫ ሆነ።
    • ፈረንሳይተደገፉት ሃይማኖቶች ተለየ።
    • ታኅሣሥ 24 ቀን - የጃፓን-ሩስያ ጦርነት፡ ጃፓን ፖርት አርሰር ከሩስያ]] ማረከ።
    • ጥር 14 ቀን - ብዙ ሰላማዊ ሰልፈኞች በሰይንት ፒተርስቡርግ ሩስያ በፖሊስ ተገደሉ።
    • የካቲት 26 ቀን - የሩስያ ሠራዊት በሙክደን ውግያ በጃፓን ተሸነፈ።
    • መጋቢት 26 ቀን - በምድር መንቀጥቀጥ በህንድ 20,000 ሰዎች ሞቱ።
    • ግንቦት 20 ቀን - ጃፓን የሩስያን መርከብ ኃይል አጠፋ።
    • ግንቦት 30 ቀን - የኖርዌይ ምክር ቤት ነጻነት ከስዊድን አዋጀ።
    • ነሐሴ 26 ቀን - በካናዳ ውስጥ አልቤርታና ሳስካቸዋን አዳዲስ ግዝቶች ሆኑ።
    • ነሐሴ 30 ቀን - ጃፓን በሩሲያ ላይ አሸንፎ በፖርትስመስ ኒው ሃምፕሽር ውል ተፈራረሙ።
  • 1899 - በአውሮፓ የተደረገ መጀመርያው የአውሮፕላን በረራ።

[ለማስተካከል] 20ኛ ምዕተ ዓመት

  • 1906 - 1ኛ አለማዊ ጦርነት በአውሮፓ ጀመረ።
  • 1907 - የደቡብ አፍሪካ ጭፍሮች ጀርመን ደቡብ-ምዕራባዊ አፍሪካ (ናሚቢያ) ወረሩ።
    • ጳጉሜ 1 ቀን - ታንክ የሚባል የጦርነት መሳርያ ለመጀመርያ ጊዜ በእንግሊዞች ተፈተነ።
  • 1911 - በሳንዠርመን ውል ዩጎስላቪያ፣ ሃንጋሪና ቸኮስሎቫኪያ ከኦስትሪያ ነጻነታቸውን አገኙ።
  • 1912 - ፖሎኝ በዋርሳው ውጊያ በሩሲያ ቀይ ጭፍሮች ላይ ያሸነፋል።
  • 1914 - ቱርኮች በግሪክ-ቱርክ ጦርነት አሸንፈው ስምርኔስ ከተማ ተቃጠለ።
  • 1915 - የእንግሊዝ አስተዳደር በፍልስጤም ጀመረ።
    • ነሐሴ 26 ቀን - ታላቅ ምድር መንቀጥቀጥ በጃፓን መቶ ሺህ የሚያህሉ ሰዎች ገደለ።
  • 1920 - ጦርነት የሚከላከል የኬሎግ-ብሪያንድ ውል በ60 አገሮች ተፈረመ።
  • - የዓለሙ መጀመርያው ቴሌቪዥን ስርጭት ፈተና ተደረገ።
  • 1921 - ሄርበርት ሁቨር የአሜሪካ ፕረዝዳንት ሆነ።
  • - የእስቶክ ገበያ ውድቀት በመከሠቱ የመላ አለም ምጣኔ ሀብት ወደ 'ታላቁ ጭፍግግ' በ1 አመት ውስጥ ቶሎ ወረደ።
  • 1924 - ጃፓን ማንቹርያን ወረረ።
  • 1931 - ሂትለርና ስታሊን በሥውር ፊርማ ፖሎኝን አካፈሉ።
    • ነሐሴ 26 ቀን - አዶልፍ ሂትለር ፖሎኝን በመውረሩ ሁለተኛ ዓለማዊ ጦርነት ጀመረ።
  • 1932 - ጀርመኖች በ2ኛ ዓለማዊ ጦርነት ለንደንን በቦምብ ለመደብደብ ጀመሩ።
  • 1934 - የአላም አል ሓልፋ ውጊያ በጀርመንና እንግሊዝ ታንኮች መኃል በግብፅ በረሃ ጀመረ።
  • 1935 - የጓደኞች ወታደርና 1,800 የጣልያ እስረኞች ተሸክማ ላኮኒያ የምትባል መርከብ አፍሪካን ስትቀርብ በጀርመኖች ተተኩሳ ሰጠመች።
    • ነሐሴ 28 ቀን - በ2ኛ አለማዊ ጦርነት ኢጣልያ በጓደኞቹ ሃያላት ተወረረች።
    • ጳጉሜ 3 ቀን - የአሜሪካ ጄኔራል አይዘንሃወር የኢጣልያ እጅ መስጠት በጦርነት አዋጀ።
  • 1936 - ፓሪስ ከተማ በጓደኞች አርበኞች ከጀርመን ነጻ ወጣች።
  • 1941 - የሶቭየት ኅብረት መጀመርያውን ንዩክሌያር መሣሪያ በፈተና አፈነዳ።
  • 1946 - የቻይና ሃያላት የደቡብ ኮርያ ደሴቶችን በቦምብ ደበደቡ።
  • 1947 - በኢስታንቡል ቱርክ በኖረበት በግሪክ ህብረተሰብ ላይ እልቂት ተደረገ።
  • 1949 - የአርካንሳው አገረ ገዥ ኦርቪል ፋውበስ ጥቁር ተማሮች ከነጭ ጋራ እንዳይማሩ የክፍላገሩን ወታደሮች በሊተል ሮክ ሰበሰበ።
  • 1951 - የቅብጥ አቡና 6ኛ ቂርሎስ ለኢትዮጵያ የራሱን አቡነ እንዲኖሩት ፈቀዱለት።
  • 1952 - መጀመርያው ሰው ሰራሽ መንኮራኩር (የሩሲያ) ጨረቃን ደረሰ።
  • 1953 - «ኦፐክ» - የዘይት አስወጪ አገሮች ድርጅት - ተመሰረተ።
  • 1954 - መጀመርያ ቴሌቪዥን ግንኙነት በአሜሪካና በአውሮጳ መካከል
  • 1955 - ዶ/ር ማርቲን ሉጠር ኪንግ «እኔ ሕልም አለኝ» ያለበትን ቃል ለሰላማዊ ሰልፍ ተናገረ።
  • 1958 - መጀመርያ የምድር ፎቶ በጨረቃ ምኋር ካለ ሰው ሰራሽ መንኮራኩር ተነሣ።
  • 1959 - ጡርጉድ ማርሻል መጀመርያ አፍሪቃ-አሜሪካዊ የዋና ብሔራዊ ችሎት ፈራጅ ተሾሙ።
  • 1960 - ፈረንሳይ ንዩክሌር ቦምብ በፈተና በመፈንዳቷ ወደ ንዩክሌር ሃያላት ገባች።
  • 1961 - መንፈቅለ መንግስት በሊቢያ ሙአማር ጋዳፊን ከፍ አደረገው።
  • 1963 - በአቲካ እስር ቤት ኒው ዮርክ ሁከት ተደረገ።
  • 1966 - ጊኔ-ቢሳው ነጻነቱን ከፖርቱጋል አገኘ።
  • 1969 - የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር የፓናማ ካናል አስተዳደር ለፓናማ በ1992 ዓ.ም. ለማዛወር ውል ፈረሙ።
  • 1970 - የጸረ-አፓርትሃይድ ወኪል ስቲቭ ቢኮ በደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ታስሮ ተገደለ።
  • 1972 - ነጻነት ለቨንዳ ተሰጠ - ይህ ግን ከደቡብ አፍሪካ ውጭ አልተቀበለም።
  • 1975 - የኮሪያ አየር መንገድ አይሮፕላን በሶቭየት ኅብረት ላይ ሲተኮስ 269 መንገደኞች ሞቱ።
  • 1978 - በመርዝ ጋዝ አደጋ በካሜሩን 1700 ሰዎች ሞቱ።
    • ጳጉሜ 2 ቀን - ዴስሞንድ ቱቱ በኤጲስቆፖሳዊ ቤተክርስቲያን በደቡብ አፍሪካ መጀመርያ ጥቁር ኤጲስ ቆጶስ ሆኑ።
  • 1979 - የሬጌ ሙዚቃ ዘፋኝ ፒተር ቶሽ ቤቱ በኪንግስተን ጃማይካ በሌቦች ተገደለ።
  • 1981 - ቮየጀር የተባለ ሰው ሰራሽ መንኮራኩር በኔፕቱን ፈልክ አለፈ።
  • 1982 - የብረት መጋረጃ በኰሙኒስት ሃንጋሪና በኦስትሪያ መሃል ተከፍቶ ወዲያው ብዙ ሺህ ጀርመኖች ወደ ምእራብ ፈለሱ።
    • ነሐሴ 22 ቀን - ሳዳም ሁሰይን ኩወይት የኢራቅ ክፍላገር ነው ይላል።
  • 1983 - ዑዝበክስታን ነጻነቱን ከሶቭየት ኅብረት አዋጀ።
  • 1984 - ፓስካል ሊሱባ በኮንጎ ሪፑብሊክ ምርጫ ፕሬዚዳንት ሆኑ፤ ይህ ምርጫ የረጅም ዘመን አንድ ፓርቲ ግዛት ጨረሰ።
  • 1985 - መይ ካሮል ጀሚሶን መጀመርያ ጥቁር አሜሪካዊት በጠፈር ሆነች።
  • 1987 - ናቶ በቦስኒያ ሰርቦች ላይ ዘመቻ ጀመረ።
  • 1988 - የራፕ ሙዚቃ ተጫዋች ቱፓክ ሻኩር በላስ ቬጋስ ተተኲሶ ተገደለ።
  • 1989 - በእስላም ታጣቂዎች በአልጄሪያ በተገረገ እልቂት 60-100 ሰዎች ተገደሉ።
  • 1990 - ስሜን ኮሪያ የራሱን ሰው ሠራሽ መንኮራኩር መጀመርያ ጊዜ ላከ።
  • 1994 - አራት አውሮፕላኖች በአረብ ታጣቂዎች ተሰርቀው በአለም ንግድ ሕንጻና በፔንታጎን ተጋጭተው 3000 ያህል ሰዎች ተገደሉ።
    • ነሐሴ 20 ቀን - የምድር ጉባኤ ስብሰባ በጆሃነስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ጀመረ።
    • ጳጉሜ 5 ቀን - ገለልተኛ አገር የሆነ ስዊስ በመጨረሻ የተባበሩት መንግስታት አባል ሆነ።
  • 1996 - ስዊድን በምርጫ ለዩሮ እምቢ አለች።

< Static Wikipedia 2008 (no images)

aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -

Static Wikipedia 2007 (no images)

aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -

Static Wikipedia 2006 (no images)

aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu

span style="font-weight: bold;">Our
"Network":



Project Gutenberg

href="https://gutenberg.classicistranieri.com">https://gutenberg.classicistranieri.com



Encyclopaedia Britannica 1911

href="https://encyclopaediabritannica.classicistranieri.com">https://encyclopaediabritannica.classicistranieri.com



Librivox Audiobooks

href="https://librivox.classicistranieri.com">https://librivox.classicistranieri.com



Linux Distributions

https://old.classicistranieri.com



Magnatune (MP3 Music)

href="https://magnatune.classicistranieri.com">https://magnatune.classicistranieri.com



Static Wikipedia (June 2008)

href="https://wikipedia.classicistranieri.com">https://wikipedia.classicistranieri.com



Static Wikipedia (March 2008)

href="https://wikipedia2007.classicistranieri.com/mar2008/">https://wikipedia2007.classicistranieri.com/mar2008/



Static Wikipedia (2007)

href="https://wikipedia2007.classicistranieri.com">https://wikipedia2007.classicistranieri.com



Static Wikipedia (2006)

href="https://wikipedia2006.classicistranieri.com">https://wikipedia2006.classicistranieri.com



Liber Liber

href="https://liberliber.classicistranieri.com">https://liberliber.classicistranieri.com



ZIM Files for Kiwix

https://zim.classicistranieri.com





Other Websites:



Bach - Goldberg Variations

https://www.goldbergvariations.org



Lazarillo de Tormes

https://www.lazarillodetormes.org



Madame Bovary

https://www.madamebovary.org



Il Fu Mattia Pascal

https://www.mattiapascal.it



The Voice in the Desert

https://www.thevoiceinthedesert.org



Confessione d'un amore fascista

https://www.amorefascista.it



Malinverno

https://www.malinverno.org



Debito formativo

https://www.debitoformativo.it



Adina Spire

https://www.adinaspire.com




atOptions = { 'key' : 'e601ada261982ce717a58b61cd5b0eaa', 'format' : 'iframe', 'height' : 60, 'width' : 468, 'params' : {} };

Our "Network":

Project Gutenberg
https://gutenberg.classicistranieri.com

Encyclopaedia Britannica 1911
https://encyclopaediabritannica.classicistranieri.com

Librivox Audiobooks
https://librivox.classicistranieri.com

Linux Distributions
https://old.classicistranieri.com

Magnatune (MP3 Music)
https://magnatune.classicistranieri.com

Static Wikipedia (June 2008)
https://wikipedia.classicistranieri.com

Static Wikipedia (March 2008)
https://wikipedia2007.classicistranieri.com/mar2008/

Static Wikipedia (2007)
https://wikipedia2007.classicistranieri.com

Static Wikipedia (2006)
https://wikipedia2006.classicistranieri.com

Liber Liber
https://liberliber.classicistranieri.com

ZIM Files for Kiwix
https://zim.classicistranieri.com


Other Websites:

Bach - Goldberg Variations
https://www.goldbergvariations.org

Lazarillo de Tormes
https://www.lazarillodetormes.org

Madame Bovary
https://www.madamebovary.org

Il Fu Mattia Pascal
https://www.mattiapascal.it

The Voice in the Desert
https://www.thevoiceinthedesert.org

Confessione d'un amore fascista
https://www.amorefascista.it

Malinverno
https://www.malinverno.org

Debito formativo
https://www.debitoformativo.it

Adina Spire
https://www.adinaspire.com