ሀራሬ
ከWikipedia
ሀራሬ (Harare) የዚምባብዌ ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢው ኗሪ ሲጨመር 2,800,111 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 1,600,000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 17°50′ ደቡብ ኬክሮስ እና 31°03′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
በ1883 ዓ.ም. በእንግሊዝ ወታደሮች ተሠርቶ ምሽግ ሆኖ ስሙ 'ፎርት ሳሊስቡሪ' ተባለ። በ1889 ዓ.ም. በምሽጉ ዙሪያ ከተማ ስላደገ ስሙ ሳሊስቡሪ ሆነ። በ1974 ዓ.ም. ስሙ ሃራሬ ሆነ።