ቱርክመንኛ
ከWikipedia
ቱርክመንኛ (Türkmen) የቱርክምኒስታን ብሔራዊ ቋንቋ ነው። በቱርክመኒስታን 3,430,000 ተናጋሪዎች ሲኖሩ ከቱርክመኒስታን ውጭ ደግሞ 3 ሚሊዮን የሚያሕሉ ተናጋሪዎች በተለይም በኢራን (2 ሚሊዮን) በአፍጋኒስታን (500,000) እና በቱርክ (1000) አሉ።
ቱርክመንኛ በቱርኪክ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ ይከተታል። ይህም አንዳንዴ በትልቁ አልታይ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ ይደመራል። ቀድሞ የተጻፈበት ወይም በቂርሎስ ወይም በ አረብ ፊደሎች ነበር፤ አሁን ግን የቱርክመኒስታን መሪ ሳፓርሙራት ኒያዞቭ በላቲን ፊደል እንዲጻፍ አዋጀ። በ1994 አ.ም. ደግሞ የሳምንት ቀኖችና የወር ስሞች ሁሉ እንደ አቶ ኒያዞቭ "ሩህናማ" የሚባል ይፋዊ መጽሐፍ ፍልስፍና በአዋጅ ተቀየሩ።
[ለማስተካከል] ተውላጠ ስም
- እኔ - men መን፣ እኔን - meni መኒ፣ የኔ - meniň መኒንግ፣
- ለኔ - maňa ማንጋ፣ በኔ - mende መንዴ፣ ከኔ - menden መንደን፣
- አንተ / አንቺ - sen ሰን፣ አንተን - seni ሰኒ፣ ያንተ - seniň ሰኒንግ፣
- ላንተ - saňa ሳንጋ፣ ባንተ - sende ሰንዴ፣ ካንተ - senden ሰንደን ፣
- እሱ / እሷ - ol ኦል፣ እሱን - ony ኦኒው፣ የሱ - onyň ኦኒውንግ፣
- ለሱ - oňa ኦንጋ፣ በሱ - onda ኦንዳ፣ ከሱ - ondan ኦንዳን፣
- እኛ - biz ቢዝ፣ እኛን - bizi ቢዚ፣ የኛ - biziň ቢዚንግ፣
- ለኛ - bize ቢዜ፣ በኛ - bizde ቢዝዴ፣ ከኛ - bizden ቢዝደን፣
- እናንተ / እርስዎ- siz ሲዝ፣ እናንተን - sizi ሲዚ፣ የናንተ - siziň ሲዚንግ፣
- ለናንተ - size ሲዜ፣ በናንተ - sizde ሲዝዴ፣ ከናንተ - sizden ሲዝደን፣
- እነሱ - olar ኦላር፣ እነሱን - olary ኦላሪው፣ የነሱ - olaryň ኦላሪውንግ፣
- ለነሱ - olara ኦላራ፣ በነሱ - olarda ኦላርዳ ፣ ከነሱ - olardan ኦላርዳን።