Web Analytics Made Easy - Statcounter

See also ebooksgratis.com: no banners, no cookies, totally FREE.

CLASSICISTRANIERI HOME PAGE - YOUTUBE CHANNEL
Privacy Policy Cookie Policy Terms and Conditions
Wikipedia - ሱሳ

ሱሳ

ከWikipedia

ባለ-ክንፍ እስፊንክስ - ከታላቁ ዳርዮስ ቤተ መንግሥት በሱሳ።
ባለ-ክንፍ እስፊንክስ - ከታላቁ ዳርዮስ ቤተ መንግሥት በሱሳ።

ሱሳ (ፋርስኛ፦ شوش /ሹሽ/፤ ዕብራይስጥשושן /ሹሻን/፤ ጥንታዊ ግሪክ፦ Σέλεύχεια /ሰለውከያ/፤ ሮማይስጥ፦ Seleucia ad Eulaeum /ሰለውኪያ አድ ኤውላዩም/) በኢራን በ32°18922′ ሰሜን ኬክሮስ እና 48°25778′ ምሥራቅ ኬንትሮስ የሚገኝ እጅግ ጥንታዊ ከተማ ነው። በ1997 ዓ.ም. 64,960 ገደማ ሰዎች ይኖሩበት ነበር[1]

ይዞታ

[ለማስተካከል] በታሪክ

ሱሳ በድሮ ጊዜ የኤላም መንግሥት ዋና ከተማ ነበረ። በዓለሙ ከሁሉ ጥንታዊ ከተሞች አንድ ነው። በኤላምኛ ከተማው ሹሻን ተባለ። በሱመርኛ መዝገቦች ይታወቃል። ለምሳሌ ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለው ትውፊት ለኡሩክ አምላክ ለኢናና እጅ የሰጠ ቦታ ይባላል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ሱሳ (ወይም 'ሱሳ ግንብ') በተለይ በመጽሐፈ አስቴር ሲጠቀስ ደግሞ አንዴ በመጽሐፈ ነህምያ አንዴም በመጽሐፈ ዳንኤል ስሙ ይገኛል። ዳንኤልና ነህምያ ሁለቱ በ6ኛ ክፍለ ዘመን ክ.በ. በባቢሎን ምርኮ ጊዜ በሱሳ ይኖሩ ነበር። አስቴርም እዚያ ንግሥት ሆና አይሁዶች ከእልቂጥ እንዲያመልጡ ቻለች። ከዚህ በላይ የነቢዩ ዳንኤል መቃብር በከተማው አካባቢ እንዳለ ይታመናል።

ሱሳ እንደገና በመጽሐፈ ኩፋሌ ይጠቀሳል። በቁ. 9፡10 እና 9፡16 መሠረት በሴምና በበኩሩ በኤላም ርስት ውስጥ ካሉት ቦታዎች አንድ ነው ይላል። በተጨማሪም በምዕ. 8፡34 'ሱስን' የኤላም ልጅ ይባላል።

በ2330 ክ.በ. ገደማ ሱሳ በ1 ሳርጎን ወደአካድ መንግሥት ተጨመረ። በአካድ ውስጥ የክፍላገሩ ዋና ከተማ ሆኖ ቀረ። በ2240 ገደማ ግን ኤላማዊው አገረ ገዡ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ በአመጽ ተነሥቶ ነጻ አወጣው። ከዚህ በኋላ ግን የኡር አዲስ መንግሥት ከተማውን ይዞት እንዲህ የኡር መንግስት በኤላማውያን እጅ እስከ ወደቀ ድረስ እስከ2012 ቆየ። ያንጊዜ ሱሳ ዳግመኛ የኤላም ዋና ከተማ ሆነ።

በ1183 ክ.በ. ግን በንጉሳቸው ሹትሩክ-ናሑንተ መሪነት ኤላማውያን የባቢሎን ንጉስ የሐሙራቢ ሕገጋት የተቀረጹበት ጽላት በዝብዘው ወደ ሱሳ በምርኮ ወሰዱት። እዚያም በ1894] ዓ.ም. ይገኝ ነበር። ይሁንና የባቢሎን ንጉስ 1 ናቦከደነጾር ከአምሳ አመት ያሕል በኋላ ሱሳን በሱ ተራ ለመበዝበዝ በቃ።

በዚህ ቅርጽ የአስናፈር ግፈኛ ዘመቻ በ655 ክ.በ. ይታያል። ነበልባል ከከተማው እየተነሣ የአሦር ሠራዊት ሲያጠፉና ምርኮውን ሲበዘብዙ ነው።
በዚህ ቅርጽ የአስናፈር ግፈኛ ዘመቻ በ655 ክ.በ. ይታያል። ነበልባል ከከተማው እየተነሣ የአሦር ሠራዊት ሲያጠፉና ምርኮውን ሲበዘብዙ ነው።

በ655 አመት ከክርስቶስ በፊት የአሦር ንጉስ አስናፈር በጦርነት ከተማውን ፈጽሞ አጠፋ። በኋላ በ545 ክ.በ. የፋርስ ንጉሥ ታላቁ ቂሮስ ከተማውን ማረከ። በቂሮስም ልጅ በካምቡሴስ ዘመን ዋና ከተማው ከፓሳርጋዳስ እስከ ሱሳ ተዛወረ።

በ339 ክ.በ. የመቄዶን ንጉሥ ታላቁ እስክንድር ከፋርስ መንግሥት ጋር ሱሳን አሸነፈው። ከሱ በኋላ ሱሳ ለሴሌውቅያ መንግሥት ስለ ታደለ ስሙ ሰለውከያ ሆነ። ከመቶ አመት በኋላ የጳርቴ መንግሥት ነጻነቱን ከሴሌውቅያ አገኝቶ ሱሳና ካሲፍያ ሁለቱ ዋና ከተሞቹ ሆኑ። የሮማ ንጉስ ትራያን በ108 ዓ.ም. ሱሳን ይዞ በአመጽ ምክንያት ቶሎ መመለስ ነበረበት። ይህም ሮማውያን ከሁሉ ወደ ምሥራቅ የደረሱበት ወቅት ነበረ።

እስላም ሰራዊቶች በ630 ዓ.ም. ፋርስን በወረሩበት ጊዜ ሱሳ እንደገና በጥፋት ላይ ተጣለ። በሌላ ዘመን በ1210 ዓ.ም. በወራሪ ሞንጎሎች እጅ በፍጹም ጠፋች።

[ለማስተካከል] የዛሬው ከተማ

ሱሳ ወይም ሹሽ ዛሬ በፋርስ ውስጥ በሑዚስታን ክፍላገር ይገኛል።

ሥፍራው በሥነ ቅርስ ረገድ አይነተኛ ቢሆንም በቅርቡ የሕገ ወጥ ቆፈራ ትልቅ ችግር ሆኖአል። [2]

ከቅርሶቹም በላይ ሱሳ ስለነቢዩም ድንኤል ስመ ጥሩ ሆኖ የሺዓ እስላም ወገንም ሆነ የፋርስ አይሁዶች መቃብሩን በጣም ያከብሩታሉ።

[ለማስተካከል] ምንጮችና ነጥቦች

[ለማስተካከል] የውጭ መያያዣዎች

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Susa የሚነኩ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።


aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -