የሥነ፡ልቡና ትምህርት
ከWikipedia
ይዞታ |
[ለማስተካከል] ታሪክ
በሙት ባሕር እስራኤል በተገኙት ብራና ጥቅሎች በአንዱ "የሥርዓት መመሪያ መጽሐፍ" በተባለ ብራና ውስጥ ለሰዎች ሁሉ ሁለት መናፍስት እንደተሾሙ ይላል፤ እነርሱም ሀሠት ወይም ትእቢት (ጥላ) እና እውነት ወይም ኅሊና (ብርሃን) ይባላሉ። ለዚህ እምነት በቤተ እስራኤል ዘንድ ተመሳሳይ ጽሁፍ አለ፤ የተሾሙ መላእክት በጐ ወይም ጥፉ አድራጎት በወርቅ ይመዝገባሉ ይላል።
በዘመናዊ ሥነ ልቡና ደግሞ አእምሮ በሁለት ክፍሎች ይለያል። አንዱ ክፍል በደረታቸው የሚስቡ እንስሳት ባይኖራቸው የሚጠቡ እንስሶች ብቻ ይዘውት ነው። ሌላው ክፍል ለእንስሳት ሁሉ የጋራ ነው።
[ለማስተካከል] የሥነ-ልቡና ጥናት መርሆዎች
የሰው ዘር ከአብዛኛው እንስሳ ለየት የሚለው እያንዳንዱ የሚያስበው ነገር የተለያየ መሆኑ ነው። እንስሶች ያውም የአዕምሮአቸው ክብደት በጣም ዝቅተኛ የሆኑ ብቻ ናቸው አንድ ነገር ላይ አተኩረው ወይም አንዱን ተከትለው የሚሄዱት። አንዳንድ የአሳ ዘሮች፤ አንዳንድ የወፍ ዘሮች፤ በመጠኑ እንደ በግ ያሉ እንስሳዎች እንደምሳሌ ይጠቀሳሉ። ሰውን በቡድን መድቦ ይሄ እንዲህ ያስባል፤ ያ እንዲያ ያስባል ማለት የሰውን ልጅ አዕምሮ ረቂቅነት አለመገንዘብ ነው።