Web Analytics Made Easy - Statcounter

See also ebooksgratis.com: no banners, no cookies, totally FREE.

CLASSICISTRANIERI HOME PAGE - YOUTUBE CHANNEL
Privacy Policy Cookie Policy Terms and Conditions
Wikipedia - ተረት ደ

ተረት ደ

ከWikipedia

  • ደሀ ሰው ዶሮ ካረደ ከሁለት አንዳቸው ቢታመሙ ነው
  • ደህና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ
  • ደህና ወገን ያጣ ወየው ያለበት ጣጣ
  • ደህና ጦር ያለው ለግምብ ይሞክረው
  • ደመና ለዝናብ ድግስ ለሆዳም
  • ደመና በሰማይ የጨዋ ልጅ በአደባባይ
  • ደመናን የጨበጠ ሰማይን የቧጠጠ የለም
  • ደመወዙ ስንዴ ስራው ምን ግዴ
  • ደመወዝ ያጣ ሎሌ ይኮበልላል በሀምሌ
  • ደም ቢያለቅሱ ድንጋይ ቢነክሱ
  • ደም ተቀብቶ ዝንብ አይፈሩም
  • ደም ተቃብቶ ዝንብ አይፈሩም
  • ደም ተበክለህ ዝንብን አትጥላ
  • ደም ከውሀ ይቀጥናል
  • ደም ካልፈሰሰ ስርየት የለም
  • ደሞዝተኛ አርፈህ ተኛ
  • ደረስሁ ልጅ ፈላሁ ጠጅ
  • ደረቅ ይቀመጠላል እርጥብ ይጎብጣል
  • ደረቴን ቢያመኝ እግሬን አገመኝ
  • ደረቴን ሲያመኝ እግሬን አገመኝ
  • ደረጃ ለፍቶ መሄጃ
  • ደስታና መከራ ቀኝና ግራ
  • ደስታና መከራ ቀኝና ግራ ናቸው
  • ደባ ራሱን ስለት ድጉሱን
  • ደባ ራሱን ስለት ድጉሱን አያጣውም
  • ደባል ሲስነብት ይሆናል ባለቤት
  • ደባልና ሹመት ያለሰበብ አይሄድ
  • ደብር ለላስታ ድግድግታ ለጌታ
  • ደብተራ ሲኮራ እቤት ክርስቶያን ገብቶ ጭራ ይይዛል
  • ደብተራ የዘኬ ጎተራ
  • ደብተራ የዘኬ ጎተራ ዘኬውን ሲቋ ጥር አነቀው ነብር
  • ደብተራና ተማሪ ሰናፊልና ሱሪ
  • ደንቆሮ ከሚያጫውተኝ የሚሰማ ያውጋኝ
  • ደንቆሮ የሰማ ለት ያብዳል
  • ደወል ላንበሳ ባማረለት ታዲያ ማን ይሰርለት
  • ደወል እንደ ጠዋቱ ትጮሀ ለች
  • ደጃቸውን አይዘጉ ሰውን ሌባ ይላሉ
  • ደጃቸውን ከፍተው ሰውን ሌባ ይላሉ
  • ደጃፉን ጥሎ በጓሮ ይመጣል
  • ደገኛ ሲያርስ ቆለኛ ያነፍስ
  • ደጉ ነገር ሳያልቅ ክፉ መናገር
  • ደግ ሰው ከንጀራው ቆርሶ ከወጡ አጥቅሶ
  • ደግ ሳይበላ ክፉ ይመራ
  • ደግ ጌታ ሲለግስ እንደ ፏፏቴ ያርስ
  • ደግ ጎረቤት ውሻና ድመት ያሳድጋል
  • ደግና ማለፊያ ትግልና ልፊያ
  • ደግ አማችን መጦር ክፉ አማችን በጦር
  • ደግ አባት እርስት ያቆማል ክፉ አባት እዳ ያቆያል
  • ደግነት አይታረስ ልጅነት አይመለስ
  • ደግ ጎረቤት እቃ አያስገዛም
  • ደግ ጎረቤት ያወጣል ከመአት
  • ደካማ ቀበሌ በአህያ ይወረራል
  • ደፋር ሴት ጉልቻ ረግጣ ትወጣለች
  • ደፋር ወጥ ያውቃል
  • ደፋርና ጭስ መውጫ ቀዳዳ አያጣም
  • ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም
  • ደፋርና ጭስ ምን ያመጣሉ
  • ደፋርና ጭስ ዝዋይ ገቡ
  • ዱርዬ ያገባ በሬው በሰኔ ገደል የገባ
  • ዱላ ለባለጌ ምርኩዝ ለአሮጌ
  • ዱላ የሚጠላው ሸክላ ብቻ ነው
  • ዱላን ይዞ ሌባን መጠየቅ
  • ዱላ ይዞ ሌባን መጠየቅ
  • ዱባ ባገሩ ጋን ያህላል አሉ
  • ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል
  • ዱባና ቅል አበቃቀሉ አንድ ይመስላል አበላሉ ለየቅሉ
  • ዱባና ቅል አብሮ ይበቅል አበላሉ ለየቅል
  • ዱቄት ባመድ ይስቃል
  • ዱጨት ባመድ ይስቃል
  • ዲያቆን ሲጠግብ በጧፍ ይማታል ወይፈን ሲቦርቅ ድንበር ያፈርሳል
  • ዲያቆን ከዘፈነ ፍየል ከቀዘነ
  • ዲያቆን ከዘፈነ ፍየል ከቀዘነ መዳኛም የለው
  • ዲያቢሎስ በክፋቱ ተወጋ ዳቢቱ
  • ዳሩ ምን ይሆናል ሆነና ሆነና
  • ዳር ሲፈታ መሀል ዳር ይሆናል
  • ዳር ዳር ያለ በመሀል የከበረ
  • ዳቦ ሲበሉ ልብ ልቡን ዳገት ሲወጡ ጥግ ጥጉን
  • ዳቦ በገና ቡና በጀበና
  • ዳቦ በወጥ በግዜር ማምለጥ
  • ዳቦ ካልበሉት ድንጋይ ሎሚ ካልመጠጡት እንቧይ
  • ዳቦ ያለ ቅርፊት ጠላ ያለ ምርጊት
  • ዳቦውን ጎርሶ ደሙን አብሶ
  • ዳተኛ በሬ ሀብታም ነው
  • ዳኛ ለዳኛ ያወርሳል ጉም ተራራ ያለብሳል
  • ዳኛ ምን ያደላ ከተረታ ሊበላ
  • ዳኛ ምን ያደላ ከተረታው ሊበላ
  • ዳኛ ሲመረምር ከራስ ይዞ እስከ እግር
  • ዳኛ ሲቆጣ ማር ይዞ ከደጁ
  • ዳኛ ሲያዳላ በዳኛ አህያ ሲያጋድል በመጫኛ
  • ዳኛ ሳለ ተናገር ውሀ ሲጠራ ተሻገር
  • ዳኛ ሲገኝ ተናገር ውሀ ሲጠራ ተሻገር
  • ዳኛ ስበር በእጅ ክበር
  • ዳኛ ቢንቁ የተያዘ እህልን ይወቁ
  • ዳኛ ቢንቁ የተያዘ እህል ይወቁ
  • ዳኛ ቢያዳላ በዳኛ አህያ ቢያጋድል በመጫኛ
  • ዳኛ ቢያጋድል በዳኛ አህያ ቢያጋድል በመጫኛ
  • ዳኛ አውጥቼ ዘንግ አቅንቼ
  • ዳኛ አይነቀፍ እሳት አይታቀፍ
  • ዳኛ ካዳላ ጭነት ቀላል
  • ዳኛ የወል ምሰሶ የመካከል
  • ዳኛ የወል ምሰሶ የማሃል
  • ዳኛ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት
  • ዳኛ የፈረደው ስለት የቀደደው
  • ዳኛ ያደላበት እሳት የበላበት
  • ዳኛ ያፈሰሱለት ፈረስ የከሰከሱለት
  • ዳኛ ይመረምራል ጣዝማ ይሰረስራል
  • ዳኛና በሬ ሀብታም ነው
  • ዳኛ ፍርድ አይከላ እህል ጎታ ይሞላ
  • ዳኛን ቢንቁ የተያዘ እህልን ይወቁ
  • ዳኞች ከመረመሩ ይናገራል ምድሩ
  • ዳኞች ከመረመሩ ይናገራል ምድሩ ይገናል ነገሩ
  • ዳኞች ከመረመሩ ይገኛል ነገሩ
  • ዳዊትን ያህል መዝሙር ጨለማን ያህል ጥቁር (የለም)
  • ዳክዬን ከውሀው ፈረስን ከገለባው
  • ዳኛ ሲገኝ ተናገር ውሀ ሲጠራ ተሻገር
  • ዳገት ሲወጡ ጥግ ጥጉን ዳቦ ሲበሉ ልብ ልቡን
  • ዳገት እርሙ ሜዳ ወንድሙ
  • ድሀ ለወዳጁ አይሰንፍ ሀብታም ካለወዳጁ አይተርፍ
  • ድሀ ሲቀልጥ አመድ አመድ ይሸታል
  • ድሀ ሲቀመጥ እጁን ይዘህ አወዛውዘው
  • ድሀ ሲቀማጠል ከወገቡ ቀምጠል
  • ድሀ ሲቀማጠል ከወገቡ ቅምጥል
  • ድሀ ሲቆጣ እግሩ ይፈናጠራል
  • ድሀ ሲቆጣ እግሩ መንገድ ያሰልጣል
  • ድሀ ሲቆጣ ከንፈሩ ያብጣል መንገዱን ያሰልጣል
  • ድሀ ሲቆጣ መንገድ ያፈጥነዋል
  • ድሀ ሲናገር ሬት ኮሶ ሀብታም ሲናገር የማር በሶ
  • ድሀ ሲንቀባረር ያለቀሰ ይመስላል
  • ድሀ ሲያገኝ ያጣ አይመስለውም
  • ድሀ ቅቤ ወዶ ማን ሊሸከም ነዶ
  • ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኑሮ እከክ ይወረው ነበር
  • ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ እከክ ይጨርሰው ነበር
  • ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ እከክ በወረሰው
  • ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ እከክ ይጨርሰው ነበር
  • ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ እከክ በፈጀው
  • ድሀ በሽታ አያውቅም ሀብታም ጤና የለውም
  • ድሀ ተበድሎ ማሩኝ ይላል ቶሎ
  • ድሀ ውሃውን ጠጥቶ እሳቱን ይሞቃል ሀብታም ስለገንዘቡ ይጨነቃል
  • ድሀና ድመት ሊሞት ሲል ያምርበታል
  • ድሀና ገበያ ሳይገናኙ ይሞታል
  • ድሀ በአመዱ ንጉስ በዘውዱ
  • ድሀ በጉልበቱ ባለጸጋ በሀብቱ
  • ድሀ ቢናገር አያደምቅ ቢጨብጥ አያጠብቅ
  • ድሀ ባይ አይኔን አመመኝ
  • ድሀ ተበድሎ ማሩኝ ይላል ቶሎ
  • ድሀ ተበድሎ ራሱ ይታረቃል ሀብታም በድሎ ተመልሶ ይስቃል
  • ድሀ ከንቡ ይዳላ
  • ድሀ ከንቡ ይዳራ
  • ድሀ ካለቀሰ ቀኑ መች አነሰ
  • ድሀ ካልሰራ ዶሮ ካልጫረ
  • ድሀ ካልጋረ ዶሮ ካልጫረ
  • ድሀ ካልዘራ ዶሮ ካልጫረ
  • ድሀ ካልዘራ ዶሮ ካልጫረ (ማን ያበላው ነበረ)
  • ድሀ ከርሻ ዳቦዬን ለማንሻ
  • ድሀ የሚበላው እንጂ የሚከፍለው አያጣም
  • ድሀ በጉልበቱ ባለጸጋ በሀ ብቱ
  • ድሀ በጉልበቱ ባለጸጋ በከብቱ
  • ድሀ ያልፍልኛል ይላል ጌታ ቀኑን ይቆጥራል
  • ድሀ ያመልክት ዳኛ ያሟግት
  • ድሀና ሹም ተሟግቶ ድንጋይና ቅል ተማትቶ የማይሆን ነው ከቶ
  • ድሀና ጌታ ተሟግቶ ድንጋይና ቅል ተማትቶ የማይሆን ነው ከቶ
  • ድሀ ምን ትሰራለህ እንጂ ምን ትበላለህ የሚለው የለም
  • ድሀ ሲያስለቅሱ ከስላሴ ይወቀሱ መንግስተ ሰማያትን አይወርሱ
  • ድሀ ቢያስለቅሱ ከስላሴ ይወቀሱ መንግስተ ሰማያትን አይወርሱ
  • ድሀን ካስለቀሱ በስላሴ ዘንድ ይወቀሱ
  • ድሀን ፈርቼ ደጄን በቀን ዘግቼ
  • ድህነት ከአምላክ መስማማት
  • ድህነት ከአምላክ መስተካከል
  • ድል በመታደል ሙያ በመጋደል
  • ድል የባለ እድል
  • ድል እድል በአንድ ድልድል
  • ድል ድል እድልህ እንዳይጎድል
  • ድመት ላመሏ ዛፍ ላይ ትወጣለች
  • ድመት መንኩሳ መናከሷን አትረሳ
  • ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ
  • ድመት በታች ከሆነች ውሻ ታሸንፋለች
  • ድመትና ቁንጫ ባዶ ቤት ይወዳል
  • ድመትና አይጥ እሳትና ጭድ
  • ድመትን በቆሎ መጠርጠር
  • ድመትን አይጥ ገደለቻት ወይ ጥቃት ወይ ጥቃት
  • ድመት ውስጥ ውስጡን አውሬ ናት
  • ድምቢጥ እንደ አቅሟ በብር ትታገማለች
  • ድምቢጥ እንደ አቅሟ በብእር ትታገማለች
  • ድምጽና ቁንጫ ባዶ ቤት ይወዳል
  • ድሪቶ ከነቅማሉ መጥፎ ሰው ከነአመሉ ወዲያ በሉ
  • ድሪያ የዝሙት ዋዜማ
  • ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
  • ድርብርብ እንደ ደጋ ንብ
  • ድርና ማግ ለሀጭና ልጋግ
  • ድር ቢያብር ጋቢ ይሰራል
  • ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
  • ድርጎ ራቱ ድርጎ ቢቀር ሞቱ
  • ድርጎ የለመደች መበለት ወተት ያየች ድመት
  • ድርጭት ፈንጠር ምዝግዝግ ጎንደር
  • ድሮም እንዳይሆን ነው የቄስ ልጅ መኮነን (አለ)
  • ድሮም እንዳይሆን ነው የቄስ ልጅ መኮንን (አለ)
  • ድሮ ካያታችን ካጤ ነው ትውልዳችን
  • ድሮም ሌባ ሲሰርቅ እንጂ ሲካፈል አይስማማም
  • ድስት ግጣሙን አያጣም
  • ድበላ አንዳንድ ጊዜ ይበላ
  • ድንቢጥ እንደ አቅሟ በብእ ር ትታገም
  • ድንቀኛ ተኳሽ ድር ይበጥሳል
  • ድንቁርና ከልብህ መካከል ተራራ ያህል
  • ድንኳን ያየ ባለጌ
  • ድንኳን ገልጦ ዙፋንን ረግጦ
  • ድንኳን ገልጦ ዙፋን ረግጦ
  • ድንኳን ገልጦ ዙፋን አጊጦ
  • ድንገተኛ ስህተት የቁልቁለት ውድቀት
  • ድንጋይ ለረገጠ ፍለጋ የለውም ውሀ ለጠጣ ሽታ የለውም
  • ድንጋይ ላይ ተቀማጭ የባለጌ ተለጣጭ
  • ድንጋይ በድንጋይ ላይ ትልቅ ቤት ይሆናል
  • ድንጋይ ቢያጎኗት ተመልሳ ካናት
  • ድንጋይ ወርዶ እዘብጥ ያርፋል ያገኘው ይተርፋል
  • ድንጋይ ሲያረጅ መጭ ያበቅላል
  • ድንጋይ ወደ ሰማይ ቢወርወር ተመልሶ ምድር
  • ድንጋይ ወደ ሰማይ ቢወርወር ተመልሶ ወደ ምድር
  • ድግርና ገባር ሲተካከል ያምር
  • ድግስ የሌለው ዋዜማ ምልክት የሌለው ዜማ
  • ድጥ ማንሸራተቱን ባለጌ ማሽሟጠጡን አይተውም
  • ዶማ ለመማሻ ማረሻ ለመፈለሻ
  • ዶሮ ላትበላው ታፈስ
  • ዶሮ ልጆቹዋን ይዛ ጓሮ ለጓሮ
  • ዶሮ ባሏ ሲሞት ሞተች እጢስ ገብታ
  • ዶሮ ሲሉ ሰምታ ሞተች እጢስ ገብታ
  • ዶሮ ሲቀጣጥቧት በመጫኛ ጣሏት
  • ዶሮ ሲደልሏት በመጫኛ ጣሏት
  • ዶሮ በልቶ ብስና ጎመን በልቶ ጤና
  • ዶሮ በልቶ ከብስና ጎመን በልቶ በጤና
  • ዶሮ በልጅዋ አንጀት ትጫወታለች
  • ዶሮ በማሰሮ ገደል ለዝንጀሮ
  • ዶሮ በጋን
  • ዶሮ ቢጠፋ ከቤቱ መነኮሰች እናቱ
  • ዶሮ ቢጠፋ ካባቱ መነኮሰች እናቱ
  • ዶሮ ቢያማት በሬ ተሳሉላት
  • ዶሮ ብታልም ጥሬዋን
  • ዶሮ ብትታመም በግ አረዱላት
  • ዶሮና ቀበሮ ተገናኝተው ጓሮ
  • ዶሮና ቀበሮ ተገናኝቶ ጓሮ
  • ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጠልፈው ጣሏት
  • ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት
  • ዶሮን ሲያታልሏት አንቺ እሩጭ እኛ እንከተልሽ አሏት
  • ዶሮን ሲያታልሏት ጥምር መንግስት አሏት
  • ዶሮን ሲያታልሏት ፎቶ አነሷት
  • ዶሮ አንዱን እንቁላል በወለደችበት ወታቦ ትሞላለች
  • ዶሮ እቤት ውላ ዝናብ ትመታለች
  • ዶሮ እኔ ባልበላው ጭሬ አላፈሰውም ወይ አለች
  • ዶሮ እኔ ባልበላ ጭሬ አላፈስም ወይ አለች
  • ዶሮ ከቆጥ በሬ ከጋጥ
  • ዶሮ ከቤት ሆና ዝናም ይመታታል
  • ዶሮ ከቤት ውላ ዝናብ ይመታታል
  • ዶሮ ከጋጥ አህያ ከቆጥ
  • ዶሮ ከጋጥ በሬ ከቆጥ
  • ዶሮ ከጮኸ ሌሊት የለም ከደብረ ታቦር ወዲያ ክረምት የለም
  • ዶሮ ከጮኸ ሌሊት ከደብረ ታቦር ወዲያ ክረምት የለም
  • ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት ከቡሄ ወዲያ የለም ክረምት
  • ዶሮ ካልበሏት አሞራ ናት
  • ዶሮ ጭራ ማረጃዋን አወጣች
  • ዶሮ ጭራ መታረጃዋን አወጣች
  • ዶሮ ጭራ የምታወጣው ምስጢር
  • ዶሮ ጭራ ጭራ አወጣች ማረጃዋን ካራ
  • ዶክተር ሲበዛ በሽተኛ ይሞታል


aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -