Web Analytics Made Easy - Statcounter

See also ebooksgratis.com: no banners, no cookies, totally FREE.

CLASSICISTRANIERI HOME PAGE - YOUTUBE CHANNEL
Privacy Policy Cookie Policy Terms and Conditions
Wikipedia - ተረት ወ

ተረት ወ

ከWikipedia

  • ወልዶ አይስም ዘርቶ አይቅም
  • ወረቱን የተቀማ ነጋዴ ዋግ የመታው ስንዴ
  • ወሬኛ ሚስት ዘርዛራ ወንፊት
  • ወራጅ ውሀ አይውሰድህ ሟች ሽማግሌ አይርገምህ
  • ወሬ ቢነግሩህ መላ ጨምር
  • ወሬ ቢያበዙት ባህያ አይጫንም
  • ወርቅ የያዘ ቀበዝባዛ እህል የያዘ ፈዛዛ
  • ወርቅ የጫነች አህያ ስትገባ የማይፈርስ ግርግዳ የለም
  • ወስፌ ቢለግም ቅቤ አይወጋም
  • ወንዝ ለወንዝ መቀደስ ያረፈ ሰይጣን መቀስቀስ
  • ወንዝ ለወንዝ ሩዋጭ የሰው በግ አራጅ
  • ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንዳባቱ ስጡት አመልማሎ ይፍተል እንደናቱ
  • ወንድ ልጅ እና ቢላዋ ጮማ ይወዳሉ
  • ወንድ ሊበላ የሴት ሌባ
  • ወንድ ልጅ በተሾመበት ሴት ልጅ ባገባበት
  • ወንድ ልጅ ለፈረስ ሴት ልጅ ለበርኖስ
  • ወንድ ልጅ አንድ ቀን እንደ አባቱ አንድ ቀን እንደ እናቱ
  • ወንድ ባለ በእለት ሴት ባለች በዓመት
  • ወንድ እንደያዙት ነው
  • ወንድ ከዋለበት ከብት ከተስማራበት
  • ወዛም ገማ ቢለው የነጭ ወሬ ነው አለው
  • ወይ አበዳሪ ወይ ተበዳሪ ይሞታል
  • ወይ አታምር ወይ አታፍር
  • ወይዘሪትነት ያንድ ቀን ርቀት
  • ወይ ዘንድሮ !አለች ቀበሮ
  • ወይኖ አረሰው ወይኖ ጎረሰው
  • ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ
  • ወደሽ ነው ቆማጢት ንጉስ ትመርቂ
  • ወደቀ ሲሉ ተሰበረ ነው
  • ወደው የዋጡት ቅልጥም ከብርንዶ ይጥም
  • ወዳጅ ይመጣል ከራያ ጠላት ይወጣል ከጉያ
  • ወገኛ ቀበሌ ወረዳ (ከፍተኛ ) መሆን ያምራታል
  • ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ
  • ወጠጤ ለወጠጤ ቢማከሩ እንዳይታረዱ
  • ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ቂጥጥ
  • ወጣ ወጣና እንደ ሸንበቆ ተገነደሰ እንደ ሙቀጫ
  • ወጥን ማን ያውቃል ቢሉ ቀላዋጭ
  • ወጥን የሚጨርስ መጎራረስ ሴትን የሚያስመታት መመላለስ
  • ወጪ ያዘዘባት ጥቁር ሴት አንገቷን ትነቀሳለች
  • ወጭትና ሴት ሲከናነቡ ይሻላል
  • ወፍ እንዳገርዋ ትጮሀለች
  • ወፍጮና ሴት መቼም አይሞላለት
  • ዋቢ ያለው ያመልጣል ዋቢ የሌለው ይሰምጣል
  • ውሀ ለሚወስደው ሰው በትርህን እንጂ እጅህን አትስጠው
  • ውሀ ለቀደመ ግዳይ ለፈለመ
  • ውሀ ለወሰደው ካሳ አይከፍልም
  • ውሀ ለወሰደው ፍለጋ የለውም
  • ውሀ ሊያንስ ሲል ይገማል ሰው ሊያንስ ሲል ይኮራል
  • ውሀ ላነቀው ባለቤቱ ላላወቀው መድሀኒት የለውም
  • ውሀ ልትቀዳ ሄዳ እንስራዋን ረስታ መጣች
  • ውሀ መልሶ ውሀ ቀልሶ
  • ውሀ መመለስ ወደ ሌላ ማፍሰስ
  • ውሀ ምን ያስጮኸዋል ድንጋይ
  • ውሀ ምን ያገሳ ድሀ ምን ያወሳ
  • ውሀ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው
  • ውሀ ሲደርቅ ይሸታል ሰው ሲከዳ ይወሸክታል
  • ውሀ ሲጎድል ተሻገር ዳኛ ሲገኝ ተናገር
  • ውሀ በለዘብታ ድንጋይ ይፈነቅላል
  • ውሀ በብልሀት ይቆላል በእሳት
  • ውሀ በእሳት ሰስ በዳገት
  • ውሀ ቢወቅጡት መልሶ እንቦጭ ነው
  • ውሀ ቢወቅጡት እንቦጭ
  • ውሀ ቢደርቅ አሳ ያልቅ
  • ውሀ ቢጠቅምህም ማእበሉን አትመኝ
  • ውሀና ገደል እያሳሳቀ ይወስዳል
  • ውሀና ጠጅ እኩል ይጠጣሉ
  • ውሀን መመለስ ወደ ሌላ ማፍሰስ
  • ውሀን ምን ያስጮኸዋል ድንጋይ
  • ውሀ አያንቅ ነገር አያልቅ
  • ውሀ እድፍን ያጠራል ትምህርት ልብን ያጠራል
  • ውሀ ከነቁ አባባ ከአጽቁ
  • ውሀ የሚወስደው ሰው አረፋ ይጨብጣል
  • ውሀ የጥቅምት ነበርሽ ታዲያ ማን ይጠጣሽ
  • ውሀ ጭስ ክፉ ሴት ሰውን ያበራሉ ከቤት
  • ውሀ ጭስና ክፉ ሴት ሰውን ያባርራሉ ከቤት
  • ውሀውም እንዳይደርቅ አሳውም እንዳያልቅ
  • ውሀውም እንዳይደርቅ አሳውም እንዳያልቅ አድርጎ ነው እርቅ
  • ውል አያወላውል ምላት አያሻግር
  • ውል ያዋውላል ታንኳ ያሻግራል
  • ውል ያዋውላል ታንኳ ያሻግራል አቧራ ያስላል
  • ውስጥ ውስጡን ድመትም አውሬ ነች
  • ውሻ ምን አገባት እርሻ
  • ውሻ በሰፈሩ ጅብ ነው
  • ውሻ በቀደደው ድመት ተከተለች
  • ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል
  • ውሻ በበላበት ይጮሀል
  • ውሻን በርግጫ ማለት እንካ ስጋ ማለት
  • ውሻ የጌታውን ጌታ አያውቅም
  • ውሽማዋን ብታይ ባልዋን ጠላች
  • ውጣ ያለው ብር ግርግዳ ሲፍቅ ያድራል
  • ውጣ ያለው ገንዘብ ግርግዳ ሲቧጥጥ ያድራል
  • ውጣ ያለው ገንዘብ ግርግዳ ሲጭር ያድራል


aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -