Web Analytics Made Easy - Statcounter

See also ebooksgratis.com: no banners, no cookies, totally FREE.

CLASSICISTRANIERI HOME PAGE - YOUTUBE CHANNEL
Privacy Policy Cookie Policy Terms and Conditions
Wikipedia - ተረት ነ

ተረት ነ

ከWikipedia

  • ነቅናቂ ሳለ ማን ጥሩ ይጠጣል
  • ነበረ እንጂ ይኖራል የሚባል ፍጡር የለም
  • ነበርንበት አትኩሩበት
  • ነቢያት በመደመዱ ሀዋርያት ገደገዱ
  • ነቢያት በቀየሱ ሀዋርያት ገሰገሱ
  • ነቢይ ቢኖር በከበረ ነበር
  • ነቢይ ባገሩ አይከበርም
  • ነብር ቢያንቀላፋ ዝንጀሮ ጎበኘው
  • ነብር ባየለበት ዘመን ድመት ይበረታል
  • ነብር ባየለበት ዘመን ድመት ይኮርታል
  • ነብር ሳይገድል ቆዳውን ያስማማል
  • ነብር አየኝ በል
  • ነብር አይኑን ታመመ ፍየል መሪ ሆነ
  • ነብር የሞተ እለት ፍየል ልጅዋን ትድራለች
  • ነዋሪ ለዘላለም አለ አምላክ የለም
  • ነውር ለባለቤቱ እንግዳ ነው
  • ነገረኛ ሰው ከቤቱ አይሞትም
  • ነገረኛ ታሞ አይተኛ
  • ነገረኛ ናቸው አርቃችሁ ቅበሩዋቸው
  • ነገረኛ ናቸው አጥልቃችሁ ቅበሩዋቸው የተነሱ እንደሆን ብዙ ነው ጣጣቸው
  • ነገረኛ ዝንጀሮ ውሻ ታረባለች
  • ነገሩ ነገር ነው ውስጡ ጥቅንጥቅ ነው
  • ነገሩ ነገር ነው ውስጡ ጉራንጉር ነው
  • ነገሩ ነው እንጅ ቢላዋ ሰው አይጎዳም
  • ነገሩ ነው እንጅ ጩቤ ሰው አይጎዳም
  • ነገሬ በሆዴ መንገዴ ባመዴ
  • ነገሬ በከንፈሬ
  • ነገር ለበለጠ ውድማ ለመለጠ
  • ነገር ለበለጥ ውድማ ለመለጥ
  • ነገር ለሰሚ ውሀ ለሎሚ
  • ነገር ለጀማሪው እሳት ለጫሪው
  • ነገር ሲበዛ ይሆናል ዋዛ
  • ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ
  • ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም
  • ነገር ሲያመልጥ እራስ ሲመልጥ አይታወቅም
  • ነገር ሲጀመር እህል ሲከመር
  • ነገር ሳያውቁ ሙግት ሳይጎለብቱ ትእቢት
  • ነገር ሳያውቁ ሙግት አቅም ሳይኖር ትእቢት
  • ነገር ስንት ነው ሁለት ምን ያበዛዋል ውሸት
  • ነገር በሆዴ መንገድ በአመዴ
  • ነገር በሆዴ እየተመኘሁ ቢከፍቱት ተልባ ሆኜ ተገኘሁ
  • ነገር በለዛው ጥሬ በለዛዛው
  • ነገር በልክ ሙያ በልብ
  • ነገር በመልከኛ ጠላ በመክደኛ
  • ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ
  • ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ መዝሙር በሀሌ
  • ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ዜማ በሀሌ
  • ነገር በቀጠሮ ዘፈን በከበሮ
  • ነገር በትኩሱ ጨዋታ በወዙ
  • ነገር በነገር ይጠቀሳል እሾህ በእሾህ ይነቀሳል
  • ነገር በእርቅ መንገድ በድርቅ
  • ነገር በእርቅ ወይፈንን በድርቅ
  • ነገር በወቀሳ በደል በካሳ
  • ነገር በዋስ እህል በነፋስ
  • ነገር በዋና ሚዶ በእረኛ
  • ነገር በዋና ሜዳ በእረና
  • ነገር በዋና ዘፈን በገና
  • ነገር በዋናው ንብ በአውራው
  • ነገር በዳኛ ሚዶ በእረኛ
  • ነገር ቢሳሳት ከጥንቱ ሰይፍ ቢመዘዝ ካፎቱ
  • ነገር ቢሳሳት ከጠዋቱ ጥጃ ቢሳሳት ከእናቱ
  • ነገር ቢበዛ ባህያ አይጫንም
  • ነገር ባዋቂ ብረት በጠራቂ
  • ነገር አለኝ ከማለት ስራ አለኝ ማለት
  • ነገርን አድምጦ እህልን አላምጦ
  • ነገር እንደዛፉ ዛፉ እንደቅርንጫፉ
  • ነገር ከመጀመሪያው እህል ከመከመሪያው
  • ነገር ከመጀመሪያ ፍለጋ ከመሻገሪያ
  • ነገር ከመጀመሪያው ውሀ ከመሻገሪያው
  • ነገር ከስነበተ ቅራሪ ከሆመጠጠ
  • ነገር ካምጩ ውሀ ከምንጩ
  • ነገር ከስሩ ውሀ ከጥሩ
  • ነገርን ከስሩ ውሀን ከጥሩ
  • ነገር ከእብድ ይገኛል
  • ነገር ከእጅ ይገኛል
  • ነገር ከዋስ ምላስ ከጥርስ
  • ነገር ከዋስ ምላስ ከጥርስ አያልፍም
  • ነገር ከውሉ ጋሻ ከንግቡ
  • ነገር ከግቡ ጋሻ ከእንግቡ
  • ነገር ከፊቱ ዱቄት ከወንፊቱ
  • ነገር ካንሹ ስጋ ከጠባሹ
  • ነገር ካንሺው ስጋ ከጠባሺው
  • ነገር ካጀማመሩ እሀ ል ካከማመሩ
  • ነገር ወዳድ ሰው ከመንገድ ዳር ቅበሩኝ ይላል
  • ነገር ወዳጅ ሰው ከመንገድ ዳር ቅበሩኝ ይላል
  • ነገር ወዳጅ ከቤቱ አይሞትም
  • ነገር ወዴት ትሄዳለህ ጎንደር መጨረሻህ ታገር
  • ነገር ያለዳኛ ትብትብ ያለመጫኛ
  • ነገር የሚከረው ጎንጓኙን ሲያገኝ ነው
  • ነገር የሻ ዳኛ አምጡ ይላል የዶሮ ሻኛ
  • ነገር የዋለበት ዳኛ ያውቃል ከብት የዋለበት እረኛ ያውቃል
  • ነገር የፈራ ይቃጠራል አውሬ የፈራ ያጥራል
  • ነገር ያለዳኛ ተረት ሰማይ ያለ ደመና ብረት
  • ነገር ፈጣሪውን እሾህ አጣሪውን
  • ነገር ነገርን ያነሳል ጥጋብ ሞትን ያስረሳል
  • ነገርህና ነገሬ ልክ ነው ሰው መስማቱ ትርፍ ነው
  • ነገር ነገርን ያመጣል ድግር አፈር(ን) ያወጣል
  • ነገርህን በጠጄ ርስትህን በልጄ
  • ነገር በነገር ይወቀሳል እሾህ በሾህ ይነቀሳል
  • ነገርም ይበረክታል ባለጋራም ይታክታል
  • ነገርኩት መስዬ እንዲመስለው ብዬ
  • ነገር መጫኛ እንዳሳጠሩት ወይም እንዳስረዘሙት ነው
  • ነገርና ገመድ አለውሉ አይፈታም
  • ነገርን በእርቅ ወይፈንን በድርቅ
  • ነገር እንዲጠፋ ዳኛውን ግደል
  • ነገር ነገርን ይወልዳል
  • ነጋሪ የሌለው ይታማ አይመስለው
  • ነጋዴ ወረቱን ዘላን ከብቱን ገበሬ ምርቱን
  • ነጋዴን ተዘማች ምን አቀላቀለው
  • ነጻነት ያኮራል ስራ ያስከብራል
  • ነጭ ሽንኩርት በመሽተቱ እራሱን ቀብሮ ይኖራል
  • ነጭ ድሀ ነጭ ማር ይከፍላል
  • ነጭ እንደሸማ ትክል እንደትርሽማ
  • ነጭ እንደሸማ ትክል እንደአክርማ
  • ነፋስ በተነሳበት ጊዜ እሳት አይጭሩም
  • ነፋስ ሲነሳ እሳት አይጫርም
  • ነፍጥ ቢያጓራ የጌታውን ጎን ይሰብር
  • ነፍጥ ቢያጓር የጌታውን ጎን ይሰብር
  • ነፍስ በፈጣሪዋ ሴት ባሳዳሪዋ
  • ኑር ባገር ጥፋ ካገር
  • ኑሮ በዘዴ አቶ ዘወልዴ
  • ኑሮ በዘዴ ጾም በሁዳዴ
  • ኑሮ በደጋ መተኛት ባልጋ
  • ኑሮ ቢያምርህ ችላ ጥጋብ ቢያምርህ ባቄላ
  • ኑሮ ከማናደድ ሄዶ መመስገን
  • ኑሮ ከማናደድ ሄዶ መናፈቅ
  • ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል
  • ኑሮ ካሉት የጤፍ ቅጠል ሁለት ሰው ያስተኛል
  • ኑሮ ካሉት ፍሪጅ ይሞቃል
  • ኑሮ ካሉት ፍሪጅ ይሞቃል አለ የቢራ ጠርሙስ
  • ኑ ባይ ከባሪ እንቢ ባይ ቀላይ
  • ኑሮ ኑሮ ከመሬት ዙሮ ዙሮ ከቤት
  • ኑሮ ኑሮ ከመሬት ዙሮ ዙሮ ከቤት አይቀርም
  • ኑሮ ያኗኑራል ህግ ያከባብራል
  • ናቂ ወዳቂ
  • ና ብላ ሳይሉት ከወጡ አውጡልኝ
  • ና ያሉት እንግዳ እራቱ ፍሪዳ
  • ናዳ መጣልህ ቢሉት ተከናንቤአለሁ አለ
  • ናዳ መጣልህ ቢሉት ተከናንቤአለሁ ልቀቀው አለ
  • ንቡን አባሮ ማሩን
  • ንብ ላጥር ሳያረዳ አይሄድም
  • ንብ ሲሰማራ አጥሩን ተመልከት
  • ንብ ቢሄድ ካጥር ሰው ቢሄድ ካገር
  • ንብ ቢሄድ ካጥር ሰው ቢሰደድ ካገር
  • ንብ ባውራው ገበሬ ባዝመራው
  • ንብን አይተህ ተገዛ ብሎዋል እግዜር
  • ንካ ያለው አይቀርም
  • ንዳማ ቢአጭዱት ክምር አይሞላም
  • ንጉሱ በድንኳናቸው እኔ በጎጆዬ
  • ንጉሱ በድንኳናቸው እኔ በጎጆዬ ንጉስ ነን አለ ድሀ
  • ንገስ ቢሉት ሳልዋጋ አልነግስ አለ
  • ንጉስ ለብያኔ አቡን ለኩነኔ
  • ንጉስ በመንግስቱ እግዜር በመለኮቱ ጎልማሳ በሚስቱ
  • ንጉስ በመንግስቱ ጎልማሳ በሚስቱ አምላክ ባምላክነቱ
  • ንጉስ በግንቡ ይታማል
  • ንጉስ በግንቡ ገበሬ በርስቱ ቢገቡባቸው ቀናተኞች ናቸው
  • ንጉስ ከግንቡ ውጭ ይታማል
  • ንጉስ በዘውዱ ድሀ ባመዱ
  • ንጉስ ቢቆጣቀስ ብለህ ውጣ
  • ንጉስ ሲቆጡ ቀስ ብላችሁ ውጡ
  • ንጉሱ ቢሞቱ ከማን ይሟገቱ
  • ንጉስ ቢያተርፍ ሁሉ ይተርፍ
  • ንጉስ ሲሞት ግንቡን ብልህ ሲሞት ልቡን
  • ንጉስ አንጋሹን ቤተክርስቲያን ቀዳሹን
  • ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ
  • ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ አባት አይወቀስ
  • ንጉሱ ከሾመው ማረሻ የሾመው
  • ንጉስ ከተነፈሰ አይን ከፈሰሰ
  • ንጉስ ከተነፈሰ ውሀ ከፈሰሰ
  • ንጉስ ይተክላል ንጉስ ይነቅላል
  • ንጉስ የቆረጠው እጅ ካለ ይቆጠራል
  • ንጉስ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት
  • ንጉስ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት (አንድ ነው)
  • ንጋትን ዶሮ ያውቃል ወፍ ያረጋግጣል
  • ንጋትን አውራ ዶሮ ያውቃል ወፍ ያረጋግጣል
  • ንጋትና ጥራት እያደር ይታያል
  • ንጉስ የሰቀለው አንበሳ የሰበረው
  • ንፉግ ለግሶ ቢሰጥ እጁ ይንቀጠቀጥ
  • ንጉስ የወደደው ዘመን የወለደው
  • ንጉስ ያላቸው ንቦች ማር ይበላሉ ንጉስ የሌላቸው ዝንቦች ጥንብን ይልሳሉ
  • ንጉስ ይሞግትልህ ንጉስ አይሞግትህ
  • ንግግር ሲበዛ ይጠፋል ማር ሲበዛ ያስተፋል
  • ንፍጥ ለባለቤቱ ቅቤ ነው
  • ኖረሽ አልጠቀምሽን ሞተሽ አለቀቅሽን
  • ኖሮ ኖሮ ከሞት ዞሮ ዞሮ ከቤት


aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -