Web Analytics Made Easy - Statcounter

See also ebooksgratis.com: no banners, no cookies, totally FREE.

CLASSICISTRANIERI HOME PAGE - YOUTUBE CHANNEL
Privacy Policy Cookie Policy Terms and Conditions
Wikipedia - ተረት ተ

ተረት ተ

ከWikipedia

  • ተሁለት ዛፍ የወደቀ
  • ተሁሉም ያው ወንድም ቢከፋም ቢበጅም
  • ተለመደና ዶሮ መከሽከሽ እኝህ እናትሽ ሀሙስ ከች
  • ተለማማጭ አልማጭ
  • ተለማበት የተጋባበት
  • ተለጣጭ የጎረቤቷን ድልህ ሟጣጭ
  • ተለጣጭ የጎረቤቷን ድልህ አሟጣጭ
  • ተላም የዋለ በሬ ተሴት የዋለ ገበሬ
  • ተላም የዋለ በሬ ከጋለሞታ የዋለ ገበሬ
  • ተሌባ ሌባ ቢሰርቀው ምን ይደንቀው
  • ተልባ መስሎሽ ሰናፍጭ ትቀምሽ
  • ተልባ በቅባ ኑግ ለሰሚው ግራ ለበይው መልካም ነው
  • ተልባ በጥባጭ ሳለች ጎመን ቀንጣሹዋን ምች መታት
  • ተልባ በጥባጭ እያለች ጎመን ቀንጣሹዋን ምች መታት
  • ተልባ ቢንጫጫ ባንድ ሙቀጫ
  • ተመልከት አላማህን ተከተል አለቃህን
  • ተመልከኛ ዳኛ መልካም ፈራጅ
  • ተመምሩ ደቀመዝሙሩ
  • ተመመራመር ይገኛል ነገር
  • ተመመራመር ይገኛል ቁምነገር
  • ተመሞት ይሻላል መስንበት
  • ተመረቅሁ ብለህ ተተረገመ አትዋል
  • ተመረቅሁ ብለህ ከተረገመ አትዋል
  • ተመርቄያለሁ ብለህ ከተረገመ አትዋል
  • ተመሮጥ ማንጋጠጥ
  • ተመሮጥ ማንጋጠጥ ይሻላል
  • ተመንግስት አመልጣለሁ ለሞት እድናለሁ ማለት ዘበት
  • ተመክሮ ልብ ተሸምቶ ድልብ አይሆንም
  • ተመዋረድ ጌታን መውደድ
  • ተሟጋች - እኔ እረታ ይመስለኛል ሰውም ይመለከተኛል
  • ተሙጃ መሀል የወጣች ቄጤማ ወይ ለወፍ ወይ ለባላ
  • ተማሪ ዘኬ ለቃሚ
  • ተማሪ ውሻ ቀባሪ
  • ተማሪና ዶሮ በሞቱ ክብሩ ነው በቁመናው እራቱ ጥሬ ነው
  • ተማሪና ዶሮ በሞቱ ክቡር ነው በቁመናው እራቱ ጥሬ ነው
  • ተማክረው የፈሱት ፈስ አይገማም
  • ተማክሮ የፈሱት ፈስ አይገማም
  • ተምሮ የማይጽፍ አክፍሎ የማይገድፍ
  • ተምሮ ያላስተማረ ዘርቶ ያላጠረ
  • ተሞተች ሚስቴ ምን አለኝ ካማቴ
  • ተሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል
  • ተረታን እንዳይሉ ይግባኝ ይላሉ
  • ተረቴን መልስ አፌን በዳቦ አብስ
  • ተረት ለነገር ይሆናል መሰረት
  • ተራራ ለጥናት ውሀ ለጥማት
  • ተራስ በላይ ንፋስ
  • ተራጋሚ ራሱን ደርጋሚ
  • ተርጅናና ተሞት ቢሸሹ አያመልጡ
  • ተሰብሮ ቢጠገን እንደነበረ አይሆን
  • ተሰብሮ ቢጠገን እንደድሮው አይሆን
  • ተሰው አለሁ ብዬ ከጅብ ተዳብዬ
  • ተሰው አለሁ ብዬ ከጅብ ጋር ተዳብዬ
  • ተሰግዳዳ ቦታ ታዳጊ ጌታ
  • ተስስታም አንድ ያንቀው አንድ ይወድቀው
  • ተስፋ መስጠት እዳ መግባት
  • ተስፋ መስጠት እያዩ እዳ መግባት
  • ተስፋ ርቆ የተሰቀለ ዳቦ ነው
  • ተስፋ ቆርጦ አንድ ላይ ከመቆም ይሻላል በተስፋ ሲጓዙ መክረም
  • ተስፋ ያልቆረጠ መነኩሴ ምናኔ ሲሄድ ሴቲቱን ይሰናበታል
  • ተስፋ ያድናል ክህደት ያመነምናል
  • ተስፋ የተሰቀለ ዳቦ ነው
  • ተሸፋፍኖ ቢተኙ ገልጦ የሚወጋ ጌታ አለ
  • ተሸፋፍኖ ቢተኙ ገልጦ የሚያይ አምላክ አለ
  • ተሹሞ ከመታለል ጥሎ መከብለል
  • ተሺ ምስክር የታቦት እግር
  • ተሻገር ከወንዙ ጉድ እንዳያበዙ
  • ተቀመጥ በወንበሬ ተናገር በከንፈሬ
  • ተቀማጭ አፉ ምላጭ
  • ተቀማጭ የሌለው ተሟጋች ስልቻ የሌለው ቧጋች
  • ተቀማጭ የሌለው ተሟጋች ስልቻ የሌለው አንጋች
  • ተቀምጠው የሰቀሉት ቆመው ለማውረድ ያስቸግራል
  • ተቀባሪ ወዲያ ማን ያርዳ
  • ተቀዳዳ ይሻላል ጨምዳዳ
  • ተቁመቱ ማጠር የልቡ መጠጠር
  • ተቁመትህ ማጠሩ ሆድህ መጠጠሩ
  • ተቁም ዶሮ ከሸክላ ማሰሮ
  • ተቂል አትጫወት አይንህን ያወጣል በእንጨት
  • ተቅበላ ጥጋብ የስቅለት ጦም ማደር ይሻላል
  • ተቆብ ላይ ሚዶ
  • ተበድሮ ቅቤ ታርዞ ጎፈሬ
  • ተባለ ቀትር አትቀታተር
  • ተባቄላ አይጠፋም ዲቃላ ከጠላ አይታጣም አተላ
  • ተተሳለ የማይበርድ ተታዘለ የማይወርድ
  • ተተናገረ አያባራ አፋቸው ከያዘ አይለቅ ምንቸታቸው
  • ተተናገረ አያባራ አፋቸው ከያዘ አይለቅ እጃቸው
  • ተተያዙ ብዙ ነው መዘዙ
  • ተተያዙ ወዲያ ቄስ ጥሩልኝ ማለት ላያደላድሉ በሺ ብር ጭነት
  • ተታመሙ መክሳት ካጡ መንጣት
  • ተናት ቀን ይሻላል
  • ተናካሽ ውሻ የጅብ መቋደሻ
  • ተናካሽ ውሻህን ተዋጊ በሬህን እሰር
  • ተናካሽ ውሻ የጅብ መደገሻ
  • ተናዞ ይሞቷል አምኖ ይሟገቷል
  • ተናገር በከንፈር ተቀመጥ በወንበር
  • ተናግሮ አናገረኝ ይወደኝ ይመስል ሄዶ ተናገረ የላክሁት ይመስል
  • ተናግሮ አናገረኝ ይወደኝ ይመስል ሄዶ ተናገረ የላኩት ይመስል
  • ተናግሮ አናግሮ የሆድን ጨርሶ ጠላት ይሆናል ወዳጅ ተመልሶ
  • ተናግሮ ከማሰብ ተከንፈር መሰብሰብ
  • ተናግሮ ከማሰብ ከንፈርን መሰብስብ
  • ተናግሮ ከመጨነቅ የቀልቀሎዬን አፉን እንቅ
  • ተናግሮ ያጣ ሰው ሶስት ጊዜ ሞቱ ነው
  • ተንከትክተሽ ስትስቂ የጥርስሽ ወገብ እንዳይቀጭ
  • ተንኮለኛ መበለት በጾም ዶሮ በፋሲካ እልበት
  • ተንኮለኛ የሰይጣን አርበኛ
  • ተንኮለኛ ተሰባብሮ ተኛ
  • ተንኮለኛ ናቸው አርቃችሁ ቅበሩዋቸው
  • ተንኮለኛ ገደል ዝንጀሮ ይጥላል በሬ ያሳልፋል
  • ተንጋሎ ቢተፉ ተመልሶ ካፉ
  • ተኚ ብልሽ አትነሺ አልኩሽ(ን)
  • ተኛ ወዲያ ጎራሽ እህል አበላሽ
  • ተከበሩ ሰው አይፈሩ
  • ተከብሮ ያደርጋል ደንቆሮ
  • ተከብት እንስት ተሀብት ርስት
  • ተከተማ ወደዱር ተአልጋ ወደምድር
  • ተከናንቦ የሚበላውን ተጎንብሰህ ግባበት
  • ተከፈት ያለው ጉሮሮ ጦም አያድርም
  • ተኩላ እንደ አንበሳ እጮህ ብላ ተተረተረች
  • ተኩላ ፍየል በላ
  • ተኩሶ ጣለ ወጋ ነቀለ
  • ተኳሽ በሁለት አይኑ አያነጣጥርም
  • ተክፉ ተወልጄ ስፈጭ አደርኩ
  • ተክፉ ጎረቤት አይሰሩም ደህና ቤት
  • ተኮሰ ጣለ ወጋ ነቀለ
  • ተወደዱ ወዲያ ገደሉ ሜዳ
  • ተወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣኦት
  • ተወገብ በላይ ጥጋብ ተወገብ በታች ራብ
  • ተወጭት አፍ የወንጭት አፋፍ
  • ተወጭት አፍ ተወንጭት አፋፍ
  • ተወፈሩ ፈጣሪን አይፈሩ ሰውን አያፍሩ
  • ተዋርዶ ከማግኘት ኮርቶ ማጣት
  • ተዋቅሶ ወዳጅነት የቂም ጠባሳ ባንገት
  • ተዋሰኝ ግዝት ይሆነኝ አበድረኝ አይማረኝ
  • ተዋጊ በሬ ተጭድ ይጣላል
  • ተዋጊ በሬህን ተናካሽ ውሻህን ያዝ
  • ተው አትርሳ ተሰርቶልሀል የሳት ገሳ
  • ተው ፈረሴን ለጉም አይዘነጉም ለሴትና ለጉም
  • ተዝካር ያየ ተማሪ ሸቀጥ ያየ አጣሪ
  • ተዝካር ያየ ተማሪ ሸቀጥ ያየ አጣሪ አይን የለውም
  • ተይዛ ትዘፍን ጦጣ
  • ተይዞ ከመለማመጥ አርፎ መቀመጥ
  • ተደርቦ መጣላት ስራ ማጣት
  • ተደብቃ ትጸንሳለች ሰው ሰብስባ ትወልዳለች
  • ተደብቃ ትጸንሳለች በሰው ስብሳብ ትወልዳለች
  • ተድረው ቢመለሱ የውሀ መንገድ ረሱ
  • ተድረው ቢመለሱ የውሀን መንገድ ረሱ
  • ተዳኛ ተሟግቶ ታዲያማ ተዋግቶ
  • ተዳኛ ተሟግቶ ላያደማ ተዋግቶ
  • ተጀመሩ መጨረስ ካራገዱ ማልቀስ
  • ተጄ በጉንጬ
  • ተገናኝተናል መሳ ለመሳ አንቺም እውር ነሽ እኔም አንካሳ
  • ተገናኝተው ሳሉ ምን ጊዜ እንገናኝ ይላሉ
  • ተገዳዩም ሟቹ ይጣደፋል
  • ተጋበዙና ብሉ ሀይ በሉ ከልክሉ
  • ተጋፊ ውሀ ሽቅብ ይሄዳል
  • ተጋፊ ውሀ አሻቅቦ ይፈሳል
  • ተግደርዳሪ ጦም አዳሪ
  • ተግደርዳሪ በልቶ ሽሮ ተበዳሪ
  • ተግደርዳሪ ቀላዋጭ ቀባጣሪ
  • ተጎሽ እበት ተንጨት ሽበት
  • ተጎንብሶ የሚበላን ተኝተህ ቀላውጠው
  • ተጠማኝ ቢሰነብት ባለርስት ይሆናል
  • ተጠንቀቅ ወደል እንዳትገባ ገደል
  • ተጥዶ የማይፈላ ተሹሞ የማይበላ
  • ተጥዶ የማይፈላ ተሹሞ የማይበላ የለም
  • ተጦረኛ ስንቅ አይደባልቁ
  • ተጦጣ የዋለ ጉሬዛ እህል ፈጅቶ ገባ
  • ተጨንቆ ኩራት ተንጠራርቶ ራት
  • ተጫውቶ መማረር አለ ጉዳይ መብረር
  • ተፈጣሪ ሙርጥ ጫሪ
  • ተፈጣሪ ይበልጣል ቂጥ ጫሪ
  • ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውም
  • ተፈጭቶ ያልተነፋ ዱቄት ተበራይቶ ያልተመረተ ምርት
  • ተፈጥሮ ሞት ተሾሞ ሸረት
  • ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውም
  • (ጠያቂ) ታድያስ (መላሽ) አለን በአዲዳስ ያውም ሳንዋስ
  • ታጥቦ ጭቃ
  • ታላቅ ወንድም እንደ አባት ይቆጠራል
  • ታላቅ ጦር ባይወጉበት ያስፈራሩበት
  • ታለቀ መቆጠብ ተሞተ መንጠብጠብ
  • ታላረፉ መከራ ነው ትርፉ
  • ታላቁን ነገር እየተመኘሁ ቢከፍቱት ተልባ ሁኘ ቀረሁ
  • ታላወቀ ዘዴ በለው በጎራዴ
  • ታልተናገሩ አይከፈት በሩ
  • ታልቸኮሉ ቀስ በቀስ ይገኛል ሁሉ
  • ታሞ የተነሳ እግዜርን ረሳ
  • ታሞ የተነሳ እግዚሄርን ረሳ
  • ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ
  • ታረጁ ወዲያ ጎፈሬ አዝመራ የሳተው ገበሬ
  • ታልጠገቡ አይዘሉ ካልዘለሉ አይሰበሩ
  • ታረጁ አይበጁ
  • ታሪክን የረሳ ስህተት መድገሙ አይቀርም ይባላል
  • ታርቄ ተመርቄ ታጥቤ ተለቃልቄ
  • ታርቆ ሙግት በልቶ ስት
  • ታሳጭ ማራኪ ይሻላል
  • ታሳጭ መካሪ ይሻላል
  • ታስሮ ከመማቀቅ ይሻላል መጠንቀቅ
  • ታቀበት በረዶ ተቁልቁለት ዘንዶ
  • ታባ ቁፍር እሸት ተበልቶለት
  • ታባቱ የተረፈ ተጠለፈ
  • ታቦተ ክፉ አጸደ መልካም
  • ታቦት በራሱ ቃጭል በጥርሱ
  • ታከረሩት ይበጠሳል
  • ታየው ትመለከተው ትታነቀው ትሞተው
  • ታዝበው ኪጠሉህ ታዝበው ይውደዱህ
  • ታዝበው ሲጠሉህ ታዝበው ይወደዱህ
  • ታዳጊ ያለው በግ ላቱን በውጭ ያሳድራል
  • ታጉል ጉልበት እዩልኝ ስሙልኝ ማለት
  • ታጉል ጥንቆላ የጨዋ ልጅ መላ
  • ታጥቦ ጭቃ
  • ታጥቀህ ታገል እንዳትንገላታ አስተውለህ ተሟገት እንዳትረታ
  • ትለብሰው የላት ትከናነበው አማራት
  • ትላንት ልጄን ዛሬ እናቴን ምን ይበጃል ዘንድሮ አለ አውራ ዶሮ
  • ትልቁ አሳ ትንሹን አሳ ይውጣል
  • ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ
  • ትልቅ ብልሀት ለንጉስ መገዛት
  • ትልቅ ብልሀት ለትምህርት መትጋት
  • ትልቅ ጥቃት ለምኖ ማጣት
  • ትልና መጋዝ በሽተኛና ጓዝ
  • ትምህርትም እንደ ኮት ፋሽኑ አለፈበት
  • ትምህርት በልጅነት አበባ በጥቅምት
  • ትምህርትን ለፈጠረ ጥይት በርጫን ላገኘ ገነት
  • ትምህርት ከሚሉት ነቀርሳ ኤድስ ከሚሉት በሽታ ያውጣን
  • ትምሀርት የማያልቅ ምርት
  • ትምህርት የማያልቅ ሀብት
  • ትሻልን ትቼ ትብስን አገባሁ
  • ትተውት የማይሄዱትን ባልንጀራ አይቀድሙትም
  • ትናንሽ ልጆች ትናንሽ ሀብቶች
  • ትንሳኤ ትንሳኤ ቢሉኝ ጸሎተ ሀሙስ መሰለኝ
  • ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ
  • ትንሽ ሰው ትንሽ ነው
  • ትንሽ ስጋ እንደ መርፌ ትወጋ
  • ትንሽ ሽሮ ባገኝ ጨው የለኝም እንጂ ተበድሬ ወጥ እሰራ ነበር
  • ትንሽ ልጅ ከሰራው ሽማግሌ የጎበኘው
  • ትንሽ ቆሎ ይዞ ካሻሮ ጠጋ
  • ትንሽ ቆሎ ያደርሳል ካሻሮ
  • ትንሽ አበላሽ
  • ትንሽ ሰው ትንሽ ነው
  • ትንሽ ጎልማሳ ትቢያ ታነሳ
  • ትንቢት ይመራል ልጓም ይገራል
  • ትንኝም ለሆዱ ዝሆንም ለሆዱ ወደ ወንዝ ወረዱ
  • ትንኝም ለሆዱ ዝሆንም ለሆዱ ተያይዘው ወደ ወንዝ ወረዱ
  • ትንሽ በመናገር እውነት ትከበር
  • ትኩስ ሬሳ ደረቁን አስነሳ
  • ትንሽ ጭላንጭል ታስይዛለች ምንጭር
  • ትእቢትን ከስስት ምን አገናኝቶት
  • ትእግስተኛ ከፈለገበት ይደርሳል
  • ትእግስት ፍራቻ አይደለም
  • ትካዜ ሲመጣ መከፋት ጓዝ ይሆናል
  • ትገርም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈሌ
  • ትጸድቅ ትኮነን ቢለው ቆይ መክሬ አስታውቅሀለሁ አለ
  • ትፈጭ የነበረች ማንጓለል አቃታት
  • ትፈጭ የነበረች ማንጓለል ተሳናት
  • ቶሎ ቶሎ ቢቆጡ አብረው አይቀመጡ
  • ቶፋ በማን ምድር ትለፋ
  • ቶፋ መቀበሪያው ያው ፈፋ


aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -