Web Analytics Made Easy - Statcounter

See also ebooksgratis.com: no banners, no cookies, totally FREE.

CLASSICISTRANIERI HOME PAGE - YOUTUBE CHANNEL
Privacy Policy Cookie Policy Terms and Conditions
Wikipedia - ተረት ለ

ተረት ለ

ከWikipedia

  • ለሀምሳ ጋን አንድ አሎሎ
  • ለሀምሳ ጋን አንድ አሎሎ ይበቃል
  • ለሀብት መትጋት ሰውነትን ያከሳል ገንዘብን ማሰብ እንቅልፍ ይነሳል
  • ለሀጥአን የወረደ ለጻድቃን ይተርፋል
  • ለሁሉም ጊዜ አለው
  • ለሂያጅ የለውም ወዳጅ
  • ለህልም ምሳሌ የለውም
  • ለሆዳም ሰው ማብላት ውቅያኖስን ለመደልደል መቃጣት
  • ለሆዳም በሬ ገለባ ያዝለታል
  • ለሆዳም በሬ ጭድ ያዝለታል
  • ለሆዳም በሬ ቫት ተከፈለ
  • ለሆዳም በቅሎ ጭድ ያዝለታል
  • ለሆዴ ጠግቤ በልብሴ አንግቤ
  • ለሆድ ቁርጠት ብላበት ለራስ ምታት ጩህበት
  • ለላሙ መንጃ ለሸማው መቅደጃ
  • ለላሙ መንጃ ለሸማው መከንጃ
  • ለላም ቀንዷ አይከብዳትም
  • ለላም ከጥጃዋና ከአላቢዋ ማን ይቀርባታል
  • ለላም የሳር ለምለም
  • ለላም ጥጃዋ ለአህያ ውርንጭላዋ
  • ለሌለው ምን ትለው
  • ለሌባ ቅሌት ልብሱ ነው
  • ለልደት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ
  • ለልጅ ሲሉ ይበሉ ለወዳጅ ሲሉ ይጠሉ
  • ለልጅ ሲሉ ይበሉ ለወገን ሲሉ ይጠሉ
  • ለልጅ አይስቁለትም ለውሻ አይሮጡለትም
  • ለልጅ ከሳቁለት ለውሻ ከሮጡለት
  • ለልጅ ጥርስህን ለዝንብ ቁስልህን
  • ለልጅ ጥርስህን ለዝንብ ቁስልህን አታሳይ
  • ለልጅ ጨዋታ ለባለጌ ቧልታ
  • ለሎሌው ምን ትለው
  • ለመሀን እምዬ ለአገልጋይ እትዬ ብርቋ ነው
  • ለመሄድና ለመላወስ አዛዥ ራስ
  • ለመሄድና ለመመለስ አዛዥ ራስ
  • ለመሆኑ ሳይሆን እንዴት ይሆናል ቢሆን
  • ለመሆን ሳይሆን እንዴት ይሆናል ቢሆን
  • ለመማር ክፍል መግባት ለመኮረጅ ካሮት መብላት
  • ለመማር ክፍል መግባት ለማለፍ ካሮት መብላት
  • ለመስማት የፈጠንህ ለመናገርና ለቁጣ የዘገየህ ሁን
  • ለመስማት የፈጠንህ ለመናገር የዘገየህ ሁን
  • ለመስራት የሚያፍር መብላት አይደፍርም
  • ለመስራት ያፈረ ለመብላት ደፈረ
  • ለመስጠት አለመቸኮል ከሰጡም ወዲያ አለመጸጸት
  • ለመነኩሴ መልካም ሎሌ
  • ለመታማት መፍራት
  • ለመከራ ያለው መነኩሴ ዳዊቱን ሸጦ አህያ ይገዛል
  • ለመከራ የጣፈው ቢነግድ አይተርፈው
  • ለሙት የለው መብት
  • ለሚመለከት ለሚያየው ሞት ቅርብ ነው
  • ለሚስት ያጎርሷል ለተመታ ይክሷል
  • ለማረም ማን ብሎት ሲሰራው ግን ግድፈት
  • ለማን አለው ፈጣሪ አለው ጠጅ ለሌለው ውሀ አለው
  • ለማን ይፈርዱ ለወደዱ አይደለም ለወለዱ
  • ለማኝ ቢያብድ ስልቻውን አይጥልም
  • ለማኝ አያማርጥም ማር አይኮመጥጥም
  • ለማየት የፈለገ አይኑን ይገልጣል
  • ለማያቅህ ታጠን ብሎሀል ሀሰን
  • ለማያውቅ ፎገራ ዱሩ ነው
  • ለማያውቁሽ ታጠኚ
  • ለማያውቁሽ ታጥበሽ ቅረቢ
  • ለማይሞት መድሀኒት አለው
  • ለማይሰጥ ሰው ስጡኝ ማለትን ማን አስተማረው
  • ለማይሰጥ ሰው ስጡኝን ማን አስተማረው
  • ለማእበል ወደብ ለነፋስ ገደብ የለውም
  • ለምሽት መብራት ለመከራ ጊዜ ብልሀት
  • ለምክንያት ምክንያት አለው
  • ለምን ላለው ፈጣሪ አለው ጠጅ ለሌለው ውሃ አለው
  • ለምን ሰርግ ይሄዳል ሰርግ አለ በቤቱ
  • ለምን ተክዤ አምላክን ይዤ
  • ለምን ያለው ስልቻውን ጫን ያለው ኮርቻውን
  • ለምን ያለው ስልቻውን ጫን ያለው ኮርቻውን አያጣም
  • ለምን ጊዜው ነቀዝሽ
  • ለምኖ ለማኝ ቆቤን ቀማኝ
  • ለሞኝ ሰኔ በጋው መስከረም ክረምቱ
  • ለሞኝ ንገረው ምን ይሰማ ብዬ ለብልህ ንገረው ምን ይሳተው ብዬ
  • ለሞኝ ንገረው ምን ይሰማ ብዬ ለብልህ ንገረው ምን ይስተው ብዬ
  • ለሞኝ ከሳቁለት ለቅዘን ከሮጡለት
  • ለሞኝ ከሳቁለት ለውሻ ከሮጡለት
  • ለሞኝ ጉድጓድ አያሳዩትም ቤት ነው ብሎ ይገባበታል
  • ለሞፈር ቆራጭ እርፍ አይታየውም በግላጭ
  • ለረዥም ሰው ልብ እና ልብስ ያጥረዋል
  • ለረዥም መንገድ አትሩጥበት ለረዥም ነገር አትቸኩልበት
  • ለራሱ አያውቅ ነዳይ ቅቤ ለመነ ላዋይ
  • ለራሱ አያውቅ ጠንቋይ መድሀኒቱ ላዋይ
  • ለራሱ ጥላ ለእግሩ ከለላ
  • ለራሱ የማይረባ ለሌላም አይረባ
  • ለራሱ የማይረባ ለሰውም አይረባ
  • ለራስ ምታት ጩህበት ለሆድ ቁርጠት ብላበት
  • ለራሱ አያውቅ ሰው አይጠይቅ
  • ለራሱ ሲቆርስ አያሳንስ
  • ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ
  • ለራስ ቢያወሩ ለቅንቅን ይዘሩ
  • ለራስ ቢያወሩ ለቅንቅን ይዘሩ አለች ዶሮ
  • ለራስ ከበጁ አይታጡ ደጁ
  • ለራበው ሰው ቆሎ ለቁልቁለት በቅሎ
  • ለራበው ባዶ መሶብ ማቅረብ
  • ለራት የማይተርፍ ዳረጎት
  • ለርስት ሴቶች ስንኳ ይሞቱበታል
  • ለሰማይ ምሰሶ የለው ለባእድ ስር የለው
  • ለሰለባ የመጣ ልብስ ቢጥሉለት አይመለስ
  • ለሰለባ የመጣ ልብስ ቢጥሉለት አይመለስም
  • ለሰበበኛ ቂጥ መረቅ አታብዛበት
  • ለሰባቂ ጆሮህን አትስጠው
  • ለሰው ልጅ ሲያበሉ ለውሻ ልጅ ያብሉ
  • ለሰው ልጅ ከሚያበሉ ለውሻ ልጅ ያብሉ
  • ለሰው ልጅ ከማብላት ለውሻ ልጅ ማብላት
  • ለሰው ልጅ እውቀት ለጦጣ ብልጠት
  • ለሰው ሞት አነሰው
  • ለሰው ሞት አነሰው ውሻውንስ ፈሴ መለሰው አለች ቀበሮ
  • ለሰው ቢነግሩት ለሰው
  • ለሰው ቢናገሩ መልሶ ለሰው ጫር ጫር አድርጌ አፈር ላልብሰው
  • ለሰው ብሎ መሞት አምላክነት ያሻል
  • ለሰው ብሎ ሲያማ ለኔ ብለህ ስማ
  • ለሰው ብትል ትጠፋለህ ለእግዜር ብትል ትለማለህ
  • ለሰው እንግዳ ላገሩ ባዳ
  • ለሰው እንዴት F አነሰው
  • ለሰው ከበሬታው ሰው ለወጥ ማጣፈጫው ጨው
  • ለሰው ጠላቱ ይወጣል ከቤቱ
  • ለሰው የማይል ሰው ሞትም ሲያንሰው
  • ለሰው ብሎ ሲያማ ለእኔ ብለህ ስማ
  • ለሴትና ለጉም አይዘነጉም
  • ለሰይጣን አትስጠው ስልጣን
  • ለእሳት ውሀ ለጸጉር ቡሀ
  • ለሴት ልጅ እስከአርባ ቀን ሞቷን ከዚያ ወዲያ ሀብቷን
  • ለሴት ምስጢር ማውራት በወንፊት መቅዳት
  • ለሴት ምክር አይገባትም
  • ለሴትና ለጉም አይዘነጉም
  • ለሴት ጠላ ለፈረስ ቆላ
  • ለስሟ መጠሪያ ቁና ሰፋች
  • ለስሱ ፍትፍት አሳይቶ እበት ያጎርሷል
  • ለሸማኔ ማገጃ ስለት ማረጃ
  • ለሹመት ካልመከሩለት ለጥርስ ካልነከሩለት
  • ለሹመት ካልመከሩለት ለጥርስ ካልከደኑለት
  • ለሹመት ያደለው የለማኝ አለቃ ይሆናል
  • ለሺ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ
  • ለቀላል ምስጢር መንገር በቀዳዳ ጤፍ መቋጠር
  • ለቀላል ሰው ምስጢር መንገር በቀዳዳ ጤፍ መቋጠር
  • ለቀላል ሰው ምስጢር መንገር በቀዳዳ አቁማዳ ጤፍ መቋጠር
  • ለቀማኛ የለውም እጅ ለበቅሎ የለውም ልጅ
  • ለቀበጠች አማት ሲሶ በትር አላት
  • ለቀባሪው አረዱት
  • ለቀን ቀጠሮ ለሴት ወይዘሮ
  • ለቀንዳም በሬ ቤት አትከልክለው ቀንዱ ይከልክለው
  • ለቀንዳም በሬ ቤት አትከልክለው ቀንዱ ይከለክለዋል
  • ለቁንጫ ለምጽ ያወጣል
  • ለቁንጫ መላላጫ
  • ለቂጡ ጨርቅ የለው ቆንጆ ያባብላል
  • ለቅልብልብ አማት ሲሶ በትር አላት
  • ለቅሶ ሳለ ከቤት ለቅሶ ይሄዳል ጎረቤት
  • ለቅሶ ሳለ ከቤት ይሄዳል ጎረቤት
  • ለቅናት የለውም ጥናት
  • ለቅዘን እግር አንስተውለት
  • ለቅዘን እግር አንስተውለት ለውሻ ሮጠውለት
  • ለቆመ ሰማይ ቅርቡ ነው
  • ለቆማጣ አንድ ጣት ብርቁ ናት
  • ለበራ ወለባ ለውሻ ገለባ
  • ለበጋ ጥጃ ውስ አነሰው ወይ
  • ለበግ ደጋ ለምቾት አልጋ
  • ለቡናሽ ቁርስ የለሽ ለነገርሽ ለዛ የለሽ
  • ለባለጌ ገድሉ ውርደቱ
  • ለቤት ሳማ ለውጭ ቄጤማ
  • ለቤት ሳንቃ ለሰው አለቃ
  • ለቤት ሳንቃ ለነገር ጠበቃ
  • ለቤት ባላ ለችግር ነጠላ
  • ለብልህ ንገረው ምን ይስተው ብዬ ለሞኝ ንገረው ምን ይገባው ብዬ
  • ለብልህ አይነግሩ ለድመት አያበሩ
  • ለብልህ አይነግሩ ላንበሳ አይመትሩ
  • ለብልህ አይነግሩ ለንጉስ አይመክሩ
  • ለብልህ አይነግሩም ለንጉስ አይመክሩም
  • ለብልህ አይነግሩ ካልጠየቀ በስተቀር
  • ለተማሪ ቆሎ ለወታደር በቅሎ
  • ለተሟጋች መዘዘኛ የዳኛ ትእግስተኛ
  • ለተረታው ያበደረ እሳት ጨመረ
  • ለተራበ ግብር ለተበደለ ነገር
  • ለተራበ በግብር ለተበደለ በነገር
  • ለተራበ ቂጣ ለተጠማ ዋንጫ
  • ለተሸሸገ ምግብ የተሸሸገ ሆድ አይጠፋለትም
  • ለተሾመ ይሟገቱለታል ለተሻረ ይመሰክሩበታል
  • ለተሾመው ይመሰክሩለታል ለተሻረው ይመሰክሩበታል
  • ለተሾመ ይመሰክሩለታል ለተሻረ ይመሰክሩበታል
  • ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው
  • ለተባባሰው ማጭድ አታውሰው
  • ለተንኮለኛ ሲሉ ይሰበስባሉ ለቅን ይፈርዳሉ
  • ለተወገረ የማያዝን እንብርት የለውም
  • ለትኋን ልጓም ማጉረስ ላፈኛ ሰው መመለስ
  • ለትኋን ልጓም ማጉረስ ላፈኛ ሰው መመለስ አይቻልም
  • ለቸኮለ ሰው ዋንጫ አስጨብጠው
  • ለችግር የፈጠረው ቢነግድ አይተርፈው
  • ለነገረኛ ሰው ጀርባህን ስጠው
  • ለነገረኛ ነገር ተውለት ለሆዳም እህል አቅርብለት
  • ለኔ ነግ በኔ
  • ለንጉስ የማይገዛ ለእግዚአብሄር አይገዛ
  • ለንጉስ ያልረዳ ከባህር የማይቀዳ
  • ለንጉስ ያልረዳ ከባህር ያልቀዳ
  • ለንፉግ ሰው የገበያ መንገድ ይጠበዋል
  • ለንፉግ ሰው የገበያ መንገድ ይጠበው
  • ለአህያ ማር አይጥማትም
  • ለአምላክ ልንገረው ለማያስቀረው
  • ለአበባ የለው ገለባ
  • ለአቤቱታ የለው ይሉኝታ
  • ለአንበሳ አታበድር ካበደርክ አትጠይቅ
  • ለአንተ ያለውን እንጀራ ይሻግታል እንጂ ማንም አይበላውም
  • ለአኩራፊ ምሳው እራት ይሆነዋል
  • ለአይነ ስውር መስተዋት
  • ለአይንና ለወዳጅ ጥቂት ይበቃል
  • ለአይን የሚከፋ ለአፍንጫ ይከረፋ
  • ለአዋጅ ነጋሪት ለጥጥ ልቃቂት
  • ለአገሩ እንግዳ ለሰው ባዳ
  • ለአፈ ግም አፍንጫ ድፍን ያዝለታል
  • ለአፉ ለከት የለውም
  • ለአፍታ የለውም ፋታ
  • ለአፍ ዳገት የለውም
  • ለእሳት እንጨት ካልነሱት አይጠፋም
  • ለእሳት እንጨት ካልነፈጉት አይጠፋም
  • ለእሳት ውሀ ለጸጉር ቡሀ
  • ለእሳት ፍላት ለጮማ ስባት
  • ለእበጥ ፍላት ለእንጨት እሳት
  • ለእባብ እግር የለው ለሞኝ መላ የለው
  • ለእብለት ስር የለው ለእባብ እግር የለው
  • ለእብለት ስር የለውም ለእባብ እግር የለውም
  • ለእበጥ ፍላት ለእንጨት እሳት
  • ለእኔ እናት ምን ደላት ያም አፈር ያም ድንጋይ ጫነባት
  • ለእውር ዝማሜ ለመላጣ ጋሜ
  • ለእውር ዝማሜ ለመላጣ ጋሜ አይስማማውም
  • ለእጅ ርቆ ለአይን ጠልቆ
  • ለእግሩ የተጠየፈ ለቂጡ አተረፈ
  • ለእግር የፈሩት ለቂጥ ይተርፋል
  • ለእግዚአብሄር የቀነቀነ ለጽድቅ ለጌታ የቀነቀነ ለወርቅ
  • ለእውነት ማማ ለውሸት ጨለማ
  • ለከለላ ጥላ ቢርብህ ብላ
  • ለከሳሽ የለው መላሽ
  • ለካህን ጥምቀት ለገበሬ ግንቦት
  • ለክፋት ያደለው አሳዳጊ የበደለው
  • ለኮ መሳቢያ ወፍጮ ማላሚያ
  • ለወሬ ሞትሁ
  • ለወሬ ሞትሁ ለእህል ሰለፍኩ
  • ለወሬ ወዳጁ ወሬ ለመነኩሴ ጥሬ
  • ለወሬ የለው ፍሬ
  • ለወሬ የለው ፍሬ ለአበባ የለው ገለባ
  • ለወሬ የቸኮለ እናቱን በመንገድ ይረዳል
  • ለወርቅ ያሉት አንገት ላሽክት
  • ለወታደር ሰፊ መንደር
  • ለወታደር ሰፊ መንደር ለወዲላ መልካም ዱላ
  • ለወይዘሮ መልካም ዶሮ
  • ለወደላ መልካም ዱላ
  • ለወዳጅ የማር ወለላ ለጠላት አሜኬላ
  • ለወዳጅና ለአይን ትንሽ ይበቃዋል
  • ለወጡም እዘኑለት ከእንጀራውም ጉረሱለት
  • ለወጡ ጊዜስ ከደረቁም
  • ለወጡም እዘኑለት ከደረቁም ብሉለት
  • ለወጥ የሚሻል ቅልውጥ
  • ለዋንጫ ቡሽ ለውሀ ጉሽ የለውም
  • ለዋስ አፍ የለው ለጉንዳን ደም የለው
  • ለውሻ ምሳ የለው ራት ብቻ
  • ለውሻ ሞት ፊት አይነጩለትም
  • ለውሻዬ ያልሁትን ልጄ ቢበላብኝ አልወድም
  • ለውሽማ ሞት ፊት አይነጩለትም
  • ለውጡኝ ባይ የሚሻለውን አውቆ
  • ለዘመዴ ያዝናል ሆዴ
  • ለዚህ ሆዴ ጠላኝ ዘመዴ
  • ለዝናም ጌታ ውሀ ነሱ
  • ለዝናም ጌታ ውሀ ነሱት
  • ለዝንብ ከትላንት ወዲያም ድሮ ነው
  • ለይቶ እንደፈፋ አንጓሎ እንዳረፋ
  • ለይቶት አባ ንጉሷ
  • ለደህና ሰው ዋጋ አነሰው
  • ለደህና ሰው ውሸት ለጅብ እሸት
  • ለደብተራ መቋሚያና ጭራ
  • ለደደብ ማስረዳት ድንጋይ ቅቤ መቀባት
  • ለደግ ንጉስ እለት እለት ማልቀስ
  • ለዳርቻው ሲሳሱ መካከሉን ተነሱ
  • ለዳርቻው ሲሳሱ ከነመሀሉም ተነሱ
  • ለዳባ ለባሽ ነገርህን አታበላሽ
  • ለዳኛ አመልክት እንዲሆን መሰረት
  • ለዳኛ የነገሩት በርጥብ ያቃጠሉት
  • ለዳኛ ዳኛ አለው ለአንበሳ ተኩላ አለው
  • ለድሀ ማን ሰጠው ውሀ
  • ለድህነት የፈጠረው ቢነግድ አይተርፈው
  • ለድህነት የፈጠረው ቢነግድ አያተርፍም
  • ለድሪ ያሉት አንገት ለአሸንክታብ
  • ለድሪ ያሉት አንገት ላሽክት
  • ለድካም የጣፈኝ ብነግድ አይተርፈኝ
  • ለዶሮ ሲነገሩ ምጥማጥ ይሰማል
  • ለጆሮ ጥርስ ለሆዳም ስስ
  • ለገላጋይ ደም የለውም
  • ለገበሬ መልካም በሬ
  • ለገቢህ ተንገብገብ
  • ለገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ
  • ለገደለ ጎፈሬ ላረጋገጠ ወሬ
  • ለገዳም የረዳ አይጎዳ
  • ለጉንዳን ደም የለው ለዝንብ ቤት የለው
  • ለጉንዳን ደም የለው ለገንዘብ ቤት የለው
  • ለጋስ ቢለግስ አበደረ እንጂ አልሰጠም
  • ለጋስ ቢለግስ አበደረ እንጂ እንዲያው አልሰጠም
  • ለእግዜር የተቀናቀነ ጽድቅ ለንጉስ የተቀናቀነ ወርቅ
  • ለጎበዝ ስጠው ሰንጋ ፈረስ
  • ለጠላትህ እንደ ዳቦ እስኪገምጥህ አትመቸው
  • ለጠቢብ አንድ ቃል ይበቃል
  • ለጠጪ ሰው የመጠጥ ወሬ አውራው
  • ለጥልና ለዳኛ ያለው ገንዘብ አፋፍ ይቆያል
  • ለጥርጣሬ ምንጣሬ
  • ለጥቅም ሲታጠቁ ከጎን ይጠንቀቁ
  • ለጥቅምት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ
  • ለውጠኝ ባይ የሚሻለውን አውቆ
  • ለጨለማ ጊዜ መብራት ለመከራ ጊዜ ብልሀት
  • ለጨቅጫቃ ሰው ከማበደር ይሻላል በጄ ማደር
  • ለጭሰኛ መሬት ለሳር ቤት ክብሪት
  • ለጾም ግድፈት ለበአል ሽረት
  • ለጾም ግድፈት ለባል ሽረት
  • ለፈረስህ አንገት ለጋሻህ እንብርት
  • ለፈሪና ለንፉግ እያደር ይቆጨዋል
  • ለፈሪ ሜዳ አይነሱም
  • ለፈሪ ምድር አይበቃውም
  • ለፈሪ ይበቃል ፍርፋሪ
  • ለፈሪ ስጠው ፍርፋሪ
  • ለፋሲካ የተዳረች ሁል ጊዜ የፋሲካ ይመስላታል
  • ለፍቅር ብተተኛ ለጠብ አረገዘች
  • ለፍቅር ብተኛት ለጠብ አረገዘች
  • ለፍቅር የለውም ድውር
  • ለፍየል ቆላ ለሙክት ባቄላ
  • ለፍየል ህመም በሬ ማረድ
  • ለፍየል ስም አውጣ ቢለው ሞት አይደርስ አለው
  • ሊበሉ የፈለጉትን አሞራ ስሙን ይሉታል ጅግራ
  • ሊበሉዋት ያሰብዋትን አሞራ ይሏታል ጂግራ
  • ሊወጋ የመጣ ጌታዬ ቢሉት አይመለስም
  • ሊያልፍ ውሀ አደረገኝ ድሀ
  • ሊያስቡት አይገድም
  • ሊጣላ የመጣ ሰብብ አያጣም
  • ላህያ ፈስ አፍንጫ አይዙለትም
  • ላህያ ማር አይጥማት
  • ላህያ ማር አይጥመውም
  • ላህያ ያልከበደው ለመጫኛ ከበደው
  • ላለው ቅንጭብ ያረግዳል
  • ላለው ይጨመርለታል
  • ላለፈ አይጸጸቱም ለሚመጣው አይበለጡም
  • ላለፈው አይጸጸቱም ለሚመጣው አይበለጡም
  • ላለፈው ክረምት ቤት አይሰራለትም
  • ላለፈው ክረምት ቤት አይሰራም
  • ላለፈው ክረምት ውሀ ማቆር አይቻልም
  • ላለፈው ጸሎት ከንቱ ጩኸት
  • ላሊበላ ሄደሽ ከህንጻው ብትሰፍሪ አይገኝም ጽድቅ አለ ባህሪ
  • ላሊበላ አደራውን አይበላ
  • ላሊበላ የቃሉን አይበላ
  • ላሊበላን ካላጠገቡት ይጮሀል ሎሌም ካልሰጡት ይከዳል
  • ላላየ ልጅ ዳቦ ፍሪዳው
  • ላላየው የሚያስገርም ለሰማው የሚያስደንቅ
  • ላላዩ ልጅ ዳቦ ፍሪዳው
  • ላላወቀው ፎገራ ዱር ነው
  • ላመት ልብስ ለእለት ጉርስ
  • ላሜ ቦራ የልጆቼን ነገር አደራ
  • ላም ሲበዘበዝ ጭራዋን ያዝ
  • ላም ቀንዷ አይከብዳትም
  • ላም በረቱን የሰው ልጅ አባቱን አይረሳም
  • ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ
  • ላም አለኝ በሰማይ ወተትዋንም አላይ
  • ላም አለኝ በሰማይ ገመድ እፈልጋለሁ
  • ላም እሳት ወለደች እንዳትልሰው ፈጃት እንዳትተወውም ልጅ ሆነባት
  • ላም ከወንዝ ልጅ ከቦዝ
  • ላንተ መምከር ጥቁር ድንጋይ ላይ ውሀ ማፍሰስ ነው
  • ላንቺ ቁምነገርሽ በሶብላ ወጥሽ
  • ላንቺ ብርቅሽ በሶቢላ ወጥሽ
  • ላያዘልቅ ጸሎት ለቅስፈት
  • ላይቀርልኝ እዳ በጊዜ ልሰናዳ
  • ሌባ ላመሉ ቅድመ እውቅና አገኘ
  • ሌባ ላመሉ ንግድ ይላል
  • ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል
  • ሌባ እናት ልጇን አታምንም
  • ሌባን ሌባ ቢሰርቀው እንዴት ይደንቀው
  • ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት
  • ልብስህን በውሀ ገንዘብህን በድሀ
  • ልብ ካላየ አይን አያይም
  • ልብ ካላየ አይን አይፈርድም
  • ልትደርቅ የደረሰች ምንጭ ጭልጭል ትላለች
  • ልትሰራ ሂዳ ተላጭታ መጣች
  • ልጅም ከሆነ ይገፋል ድንችም ከሆነ ይጠፋል
  • ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች
  • ልጅ ምን ቢሮጥ አባቱን አይቀድምም
  • ልጅ ሳለህ አጊጥ ሞል ሳይዘጋ ሸምት
  • ልጅ ቢያኮርፍ ቁርሱ እራት ይሆናል
  • ልጅና እሳት ባለቤቱ ያጠፋዋል
  • ልጅን አሳዳጊ እሳትን ውሀ ያጠፋዋል
  • ልጅና ወረቀት የያዘውን አይለቅም
  • ልጅና ጦጣ ውሀ ይጠጣ
  • ልጅ ያቦካው ለእራት አይሆንም
  • ልጅ ይወለዳል ከቦዝ ላም ይገዛል ከወንዝ
  • ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ
  • ልግመኛ ባሪያ መጇን ትደብቃለች
  • ልግመኛ አጋዥ ብታገኝ መጅ ደበቀች
  • ልግመኛን መምከር ውሀ በወንፊት ማኖር
  • ልፋት ቢያምርህ መሬት ግዛ ችግር ቢያምርህ ልጅ አብዛ
  • ልፋ ያለው ሊስትሮ እግር ስር ይውላል
  • ልፋ ያለው ምረጡኝ አለ
  • ልፋ ያለው በህልሙ ሲሸከም ያድራል
  • ልፋ ያለው በሬ ቆዳው ለከበሮ
  • ልፋ ያለው ቢን ላደንን ይፈልጋል
  • ልፋ ያለው አንድ እንጨት ያስራል
  • ሎሌ ለስህተት ጌታ ለምህረት
  • ሎሌ ሲከብር ጌታውን ይከሳል ሙክት ሲሰባ ሾተሉን ይልሳል
  • ሎሌ ሲከብር ጌታውን ይከሳል ሙክት ሲሰባ ሾተል ይልሳል
  • ሎሌ ያገለገለውን ይቆጥራል ጌታ ያስቀየመውን ያስባል
  • ሎሌና አሞሌ ካዘዙት ይውላል
  • ሎሚ ካልመጠጡት እምቧይ ነው
  • ሎሚ ካልመጠጡት እምቧይ ዳቦ ካልገመጡት ድንጋይ
  • ሎሚና ትርንጎ ሞልቶልህ ባገር እንቧይ ታሸታለህ የድሀ ነገር
  • ሎሚና ትርንጎ ሞልቶ ባገር እንቧይ ያሸታል አወይ የድሀ ነገር
  • ሎሚ ቢያብብ ቢኖርና መልካም ሽታ ቢሰጥ መኮምጠጡን አይተውም


aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -