Web Analytics Made Easy - Statcounter

See also ebooksgratis.com: no banners, no cookies, totally FREE.

CLASSICISTRANIERI HOME PAGE - YOUTUBE CHANNEL
Privacy Policy Cookie Policy Terms and Conditions
Wikipedia - ተረት ሀ

ተረት ሀ

ከWikipedia

  • ሀሜተኛ ነው ከዳተኛ
  • ሀሜተኛ ያፍራል ሀስተኛ ይረታል
  • ሀሜተኛ ያፍራል እውነተኛ ይረታል
  • ሀሜት አይቀር ከድሀም ቤት
  • ሀሜትና ጅራት በስተኋላ ነው
  • ሀምሌ ቢያባራ በጋ ይመስላል
  • ሀምሌና ሙሽራ ሳይገለጡ ነው
  • ሀምሌን በብጣሪ ነሀሴን በእንጥርጣሪ
  • ሀምሳ ሎሚ ለሀምሳ ሰው ጌጡ ለአንድ ሰው ሸክሙ
  • ሀረጉን ሲስቡት ዛፉ ይወዛወዛል
  • ሀረጉን ሳብ ዛፉ እንዲሳሳብ
  • ሀረግ ለመዳፍ አልጋ ለምንጣፍ
  • ሀሰተኛ ምስክር ጉልበት ይሰብር
  • ሀሰተኛን ሲረቱ በወንድም በእህቱ
  • ሀሰተኛ ሲናገር ይታወቃል ስሱ ሲበላ ይታነቃል
  • ሀሰተኛ ሲናገር ይታወቃል በሶ ሲበሉት ያንቃል
  • ሀሰተኛ በቃሉ ስደተኛ በቅሉ ሀሰተኛ በቃሉ ስደተኛ በቅሉ ይታወቃሉ
  • ሀሰተኛ ብርቱ ወንጀለኛ
  • ሀሰተኛ ያወራውን ፈረሰኛ አይመልሰውም
  • ሀሰት ስለበዛ እውነት ሆነ ዋዛ
  • ሀሰት ቢናገሩ ውቃቢ ይርቃል
  • ሀሰትና ስንቅ እያደረ ያልቅ
  • ሀሰት አያቀላ እውነት አያደላ
  • ሀሰት አያድንም መራቆት መልክ አያሳምርም
  • ሀስት እያደር ይቀላል እውነት እያደር ይበራል ሀስት እያደር ይቀላል እውነትና ውሀ እያደር ይጠራል
  • ሀሰት ነገር ክፉ ገሀነም እሳት ትርፉ
  • ሀሳቡ ጥልቅ ነገሩ ጥብቅ
  • ሀሳብህን ጨርቅ ያድርገው
  • ሀሳብና መንገድ ማለቂያ የለውም
  • ሀሳብ ከውለታ አይቆጠርም
  • ሀሳብ ከፊት አይፈታ ሙት አይመታ
  • ሀሳብ ያገናኛል ፍራት ያሸኛኛል
  • ሀሳብ ያገናኛል ፍርሀት ያሸኛኛል
  • ሀ ሳይሉ ጥፈት ውል ሳይዙ ሙግት
  • ሀ ባሉ ተዝካር በሉ
  • ሀ ባሉ ደሞዝ በሉ
  • ሀብታም ለሀብታም ይጠቃቀሱ ድሀ ለድሀ ይለቃቀሱ ሀብታም ለሰጠ የድሀ ሙርጥ አበጠ
  • ሀብታም ለሰጠ የድሀ ሙርጥ ያብጣል
  • ሀብታም ለሰጠ ደሀ ምንጭሩ አበጠ
  • ሀብታም ለሰጠው ደሀ ይንቀጠቀጣል
  • ሀብታም ሊሰጥ የደሀ ቂጥ ያብጥ ሀብታም ሊሰጥ የደሀው ሙርጥ ያብጣል
  • ሀብታም ሊሰጥ ደሀ ምርጥ ያወጣል
  • ሀብታም ሲወድቅ ከሰገነት ድሀ ሲወድቅ ከመሬት
  • ሀብታም በመመጽወቱ ድሀ በጸሎቱ
  • ሀብታም በከብቱ ድሀ በጉልበቱ
  • ሀብታም በወርቁ ድሀ በጨርቁ
  • ሀብታም በገንዘቡ ድሀ በጥበቡ እርስ በርስ ይቃረቡ ሀብታም በገንዘቡ ይኮራል ድሀ በጥበቡ ይከበራል
  • ሀብታም በገንዘቡ ይኮራል ድሀ በጥበቡ ይከብራል ሀብታም ቢሰጥ አበደረ እንጂ አልሰጠም
  • ሀብታም ቢያብር ድህነትን ያጠፋል
  • ብታም ነው መባል ያኮራል ድሀ ነው መባል ያሳፍራል ሀብታም እንደሚበላለት ድሀ እንደሚከናወንለት
  • ሀብታም ያለ ድሀ አይኮራም ድሀ ያለ ሀብታም አይበላም ሀብታም ገንዘቡን ያስባል ድሀ ቀኑን ይቆጥራል
  • ሀብት እና እውቀት አይገኝ (ም ) አንድነት
  • ሀብት የጠዋት ጤዛ ነው
  • ሀኪም ሲበዛ በሽተኛው ይሞታል
  • ሀኪም የያዘው ነፍስ ባያድር ይውላል
  • ሀኪሞች እስኪመካከሩ በሽተኛው ይሞታል
  • ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ
  • ሀዘንና ደስታ ጎን ለጎን ናቸው
  • ሀዘንን የፈራ በደስታ የተጣራ
  • ሀይለኛ ውሀ አሻቅቦ ይፈሳል
  • ሀይለኛ ዱቄት ከነፋስ ይጣላል
  • ሀይማኖቱ ከጅማት ጉልበቱ ከብረት የጠና
  • ሀይማኖት ከግብር ጸሎት ከፍቅር
  • ሀይማኖት ያለ ፍቅር ጸሎት ያለ ግብር
  • ሀይማኖት የሌለው ሰው ልጓም የሌለው ፈረስ ነው ሀጢአት ለሰሪው ምህረት ለአክባሪው
  • ሀጢአት ሲደጋገም ጽድቅ ይመስላል
  • ሀጢአት ሳያበዙ በጊዜ ይጓዙ
  • ሀጢአት በንስሀ በደል በካሳ
  • ሀጢአት በንስሀ እድፍ በውሀ
  • ሀፍረት ያከሳል ያመነምናል
  • ሁለተኛ ደሞ ለዘበኛ ! አሉ ሁለተኛ ግፌ ጫንቃዬን ተገርፌ ልብሴን መገፈፌ
  • ሁለተኛ ግፍ ልብሴን ይገፍ ጀርባዬን ይገርፍ
  • ሁለተኛ ጥፋት ቆሞ ማንቀላፋት ሁለተኛ ጥፋት ከገበያ ማንቀላፋት
  • ሁለተኛ ጥፋት ከገበያ ቆሞ ማንቀላፋት
  • ሁለቱን የተመኘ አንዱንም አላገኝ
  • ሁለቱን የተመኘ አንድም አላገኘ
  • ሁለቱን ወንበዴ በአንድ ዘዴ
  • ሁለቴ ሰላምታ አንዱ ለነገር ነው
  • ሁለት ሆነው የተናገሩት በመሬት የቀበሩት
  • ሁለት ሞት መጣ ቢለው አንዱን ግባ በለው አለ
  • ሁለት ሞግዚት ያለው ህጻን ያለጥርጥር በእሳት ይቃጠላል ሁለት ቁና ሰጥቼ አንድ ጥንቅል
  • ሁለት ባላ ትከል አንዱ ሲስበር ባንዱ ተንጠልጠል
  • ሁለት ባላ ትከል አንዱ ሲነቀል ካንዱ ተንጠልጠል ሁለት ብልጥ ኑግ አያደቅ
  • ሁለት አይወዱም ከመነኮሱ አይወልዱም
  • ሁለት አይወዱ ከመነኩሴ አይወልዱ
  • ሁለት አይወዱ ከመነኮሱ አይወልዱ
  • ሁለት አገር አራሽ ለባልንጀራው አውራሽ
  • ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ አይወጡም
  • ሁለት እግር አለኝ ብሎ እሁለት ዛፍ አይወጣም
  • ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም
  • ሁለት አፎች ባይናከሱ ይናቀሱ
  • ሁለት ወፎች ባይናከሱ ይናቀሱ
  • ሁለት የተመኘ አንድም አላገኘ
  • ሁለት የወደደ አንዱን ሳያገኝ ሄደ
  • ሁለት ጉድጓድ ያላት አይጥ አትሞትም
  • ሁለት ጊዜ ተናገርህ ከፋህ
  • ሁለት ጊዜ በላህ ተፋህ
  • ሁለት ጊዜ ተናግረህ ከፋህ
  • ሁለት ጊዜ በላህ ተፋህ
  • ሁለት ጊዜ ነው የዶሮ ልደት አንዱ በእንቁላል አንዱ በጫጩት
  • ሁለት ጊዜ ይፈርዱ ጉድ ይወልዱ
  • ሁለት ጥፉ ካገር ይጥፉ
  • ሁሉ ሄዶ ተበተነ እህና እኔ ቀረነ አለ እያዘነ
  • ሁሉ ሄደ ተበተነ እህና እኔ ቀረነ አለ ያዘነ
  • ሁሉ ሆነ ቃልቻ ማን ይሸከም ስልቻ
  • ሁሉም ሰው መምሰሉ ባይታይ አመሉ
  • ሁሉም ሸክሙን ፍቅርም ያዥውን
  • ሁሉም በየዘመድህ ቢሉት አክንባሎ ጋጥ ገባ
  • ሁሉም አካል ነው ግን እንደአይን አይሆንም
  • ሁሉም ከኋላው ያገኘዋል እንደስራው
  • ሁሉም ከልኩ አያልፍም
  • ሁሉም ወንፈሉን ፈታይም ድውሩን
  • ሁሉም ያልፋል እውነት ብቻ ይተርፋል
  • ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ
  • ሁሉ ቢናገር ማን ይሰማል
  • ሁሉ አማረኝን ገበያ አታውጣት
  • ሁሉ አረሰ ማን ይሸምት
  • ሁሉ የሚገኝ ከእሱ የሚገኝ የለም ያለእርሱ
  • ሁሉን ለእኔ አትበል
  • ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል
  • ሁሉን አውቆ አሳውን እሾህ ከስጋው ለይቶ
  • ሁሉ ያልፋል እስኪያልፍ ያለፋል
  • ሁሉም ያልፋል ግን እስኪያልፍ ያለፋል
  • ሁሉ ያልፋል እውነት ብቻ ይተርፋል
  • ሁሉም በየዘርህ ቢሉት አከንባሎ ጋጣ ገባ
  • ሁሉም ያልፋል የሚኮርጅም ቢሆን
  • ሁሉ አማረሽን ዲስኮ (disco) አታውጧት
  • ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት
  • ሁል ጊዜ ባሬራ ትበያለሽ ወይ አንዳንድ ጊዜ እንኳ ወጥ አትይሞይ
  • ሁል ጊዜ ከመደንገጥ አንድ ጊዜ መሸጥ
  • ሂዳ ጉበት ቢነሷት ታናሽ ታላቅ ስደዱልኝ አለች
  • ሂዳ ጉበት የነሷት ታናሽ ታላቅ ስደዱልኝ አለች
  • ሂዳ ጉበት ይነሷታል ታናሽ ታላቅ ላኩልኝ አለች
  • ሂድ አትበለው እንዲሄድ አድርገው
  • ሂድ አትበለው እንደሚሄድ አርገው
  • ሂድ ካገር ኑር ካገር
  • ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም
  • ህልም አለ ተብሎ ሳይተኛ አይታደርም
  • ህመሙ ቀርቶ ሞቱን በሰጠኝ
  • ህመሙ ቀርቶ ሞቱን በተወኝ
  • ህመሙን የሸሸገ መድሀኒት የለውም
  • ህመሙን የደበቀ መድሀኒቱም አልታወቀ
  • ህመሙን የደበቀ መድሀኒት የለውም
  • ህዳር መማረሪያ ሰኔ መቃጠሪያ
  • ህያዋን ለነገስታት ሙታን ለካህናት ይገብራሉ
  • ህግ ይኖራል ተተክሎ ስርአት ይኖራል ተዛውሮ
  • ሆሆሆ ስቄ ልሙት አለ ሰውየው
  • ሆቴል ቢያብር ገንዘብ ያስገኛል
  • ሆደ ሰፊ ነገር አሳላፊ
  • ሆደ ሰፊ ይሻላል ከአኩራፊ
  • ሆዱ ሲሞላ ፍቅሩ ሌላ
  • ሆዱ ሲጎድል ሰው ያጋድል
  • ሆዱ ናረት ሙያው ከጅረት
  • ሆዱን የወደደ ማእረጉን የጠላ
  • ሆዱን የወደደ ማእረጉን ይጠላል
  • ሆዱን ያለ ሆዱን ተወጋ
  • ሆዱ ወድዶ አፉ ክዶ ክፉ ለምዶ
  • ሆዱ ፈሪ እግሩ ዳተኛ አዳም ሲዋጋ እርሱ ይተኛ
  • ሆዳም ሰው እንብርት የለውም
  • ሆዳም ቢሸከም የበላ ይመስለዋል
  • ሆዳም ቢፈተፍት የጠገበ ይመስለዋል
  • ሆዳም ፍቅር አያውቅም
  • ሆዴ በጀርባዬ ቢሆን ገፍቶ ገደል በጣለኝ
  • ሆዴ ኑር በዘዴ
  • ሆዴን በልቶኝ ጎኔን ቢያኩኝ አይገባኝ
  • ሆዴ አታጣላኝ ከዘመዴ
  • ሆድህና ልጅህ አይጥሉህ
  • ሆድህን ጎመን ሙላው ጀርባህን ለጠላት አታሳየው
  • ሆዴ ሆዴ የሚለውን ጌታ ያየዋል አይኔ አይኔ የሚለውን ሰው ያየዋል
  • ሆድ ሆዴን የምትል ወፍ አለች ምናለች
  • ሆድ ለማታ በልቶ ለጠዋት
  • ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው
  • ሆድ ለባሰው ቢላዋ አታውሰው
  • ሆድ ለተተባሰው ማጭድ አታውሰው
  • ሆድ ሲሞላ ራስ ባዶ ይቀራል
  • ሆድ ሲያር ጥርስ ይስቃል
  • ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ
  • ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ጠዋት
  • ሆድ ባዶን ይጠላል
  • ሆድ ባዶ ይጠላል
  • ሆድ ከሁዳድ ይስፋል
  • ሆድ ካገር ይስፋል
  • ሆድ እንዳሳዩት ነው
  • ሆድና ግንባር አይሸሸጉም
  • ሆድና ግንባር አይሸሸግም
  • ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት ዳገት ላይ ይለግማል ሆድን በጎመን ቢደልሉት ይለግማል ጉልበት
  • ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል
  • ሆድ ወዶ አፍ ክዶ ክፉ ለምዶ
  • ሆድ ዘመድ ሳይወድ አፍ እህል ሳይለምድ
  • ሆድ የኔ ነው ሲሉት ቁርጠት ሆኖ ይገድላል
  • ሆድ የሸሸገውን ብቅል ያወጣዋል
  • ሆድ ያበላውን ያመሰገናል
  • ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል


aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -