Web Analytics Made Easy - Statcounter

See also ebooksgratis.com: no banners, no cookies, totally FREE.

CLASSICISTRANIERI HOME PAGE - YOUTUBE CHANNEL
Privacy Policy Cookie Policy Terms and Conditions
Wikipedia - ሃዲስ አለማየሁ

ሃዲስ አለማየሁ

ከWikipedia

ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ከአባታቸው ከቄስ አለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ አለሙ በደብረ ማርቆስ ወረዳ በእንዶር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በጥቅምት 5 ቀን 1903 ዓ.ም. ተወለዱ። ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት መከታተል ጀመሩ። የቤተክርስቲያን ስርአታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ ኤልያስ፣ በደብረ ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በሗላ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በስዊድን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በሗላም በራስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታተሉ። ለትንሽ ግዜ በአስተማሪነት ሰራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ተከሰተ።

በጦር ሜዳ ዘምተው ሲዋጉ ቆይተው በአርበኝነት ሲንቀሳቀሱ በመያዛቸው ጣሊያን ከራስ እመሩ ሀይለ ስላሴ ጋር ተልከው ለሰባት አመት በፖንዞ ደሴትና በሊፓሪ ደሴት ታስረው ቆይተዋል።

ከዚያም የታባባሪ ሃያላት ወታደሮች በ1935 ዓ.ም. ሲያመልጡዋቸው በተመለሱበት ጊዜ በትምህርታቸው እንደገና በኦክስፎርድ ከገፉ በሗላ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተለይም በትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ግዜ አገልግለዋል።

  • 1936 - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኛ
  • 1937-1938 - የኢትዮጵያ ቆንሱል በኢየሩሳሌም
  • 1938 - በ International Telecommunications Conference አትላንቲክ ከተማ፣ ኒው ጄርዚ ወኪል
  • 1938-1942 - በተባባሪ መንግሥታት ቢሮ ኒው ዮርክ ሠራተኛ
  • 1942-1948 - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳይረክተርና ምትክል
  • 1948-1952 - በተባባሪ መንግሥታት የኢትዮጵያ አምባሰደር
  • 1952 - የትምህርት ሚኒስትር
  • 1952-1957 - የኢትዮጵያ አምባሰደር ወደ እንግሊዝሆላንድ
  • 1957-1958 - የልማት ሚኒስትር
  • 1960-1966 - ሴናቶር

አዲስ አለማየሁ በርካታ የስነጽሁፍ ስራዋችን አበርክተዋል። ከነዚህም ውስጥ ታላቅ አድናቆትንና እውቅናን ያተረፈው ስራቸው ፍቅር እስከ መቃብር (1958) በሁለት የተለያዩ መደቦች ውስጥ የሚገኙ የሁለት ሰዎች የፍቅር ታሪክ ላይ ያተኩራል። እንዲሁም በ1970 ወንጀለኛው ዳኛ በ 1980 ደግሞ ስለ ማህበራዊ ጉዳዮችና ስለ ጣሊያን ውርስ የሚዳስሰውን የልም እዣት የተሰኙትን ልብ ወለድ ታሪኮች ለንባብ አቅርባዋል።

ከዚህ ባሻገር:

  • የበሻና የወደሁላ ጋብቻ
  • ተረት ተረት የመሰረት
  • ትዝታ

የተሰኙት ጽሁፎችና የሌሎች በርካታ ስራዎች ባለቤት ናቸው።

አዲስ አለማየሁ በኅዳር 26 ቀን 1996 ዓ.ም. በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

[ለማስተካከል] ዋቢ መጻሕፍት

Historical Dictionary of Ethiopia

በሌሎች ቋንቋዎች


aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -