ካቡል
ከWikipedia
ካቡል የአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 2,206,300 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 34°31′ ሰሜን ኬክሮስ እና 69°12′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
የካቡል ዕድሜ ቢያንስ 3,000 አመት ነው። ጥንታዊ ስሙ ካምቦጃፑራ ነበረ። ለፋርሶችና ለግሪኮች (300-100 ክ.በ) 'ካቡራ' ተብሎ ታወቀ። የቻይና ሊቅ ሿን ጻንግ (7ኛ ክፍለ ዘመን የኖረ) ደግሞ 'ካውፉ' ይለዋል።