አሽጋባት
ከWikipedia
አሽጋባት (Aşgabat) የቱርክሜኒስታን ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 727,700 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 37°58′ ሰሜን ኬክሮስ እና 58°24′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
አሽጋባት ከጥንታዊ ጳርቴ ሰዎች ዋና ከተማ (ክ.በ. 260 ገዳማ - ክ.በ. 15 ገዳማ) ከኒሳ ፍርስራሽ ቅርብ (18 ኪሎሜትር) ነው።
አሽጋባት መንደር ሆኖ በ1810 ዓ.ም. ተመሠረተ። ከ1909 እስከ 1919 ዓ.ም. ስሙ በሶቭየቶች ፖልቶራትስክ ተባለ። ከ1919 እስከ 1983 ድረስ በሩስኛ አሽካባድ ተባለ።