Wikipedia:ቀላል መማርያ
ከWikipedia
ሰላምታ! ዊኪፔድያ ማለት ብዙ ሰዎች አብረው በብዙ ልሣናት መዛግብተ ዕውቀት በመፍጠር እየጣሩ ነው። እዚህ ቦታ በአማርኛ ለመጻፍ የምንችልበት ዊኪፔድያ እነሆ እዚህ አለላችሁ።
ማንኛውም ሰው በኢንተርኔት ግንኙነት ካለ አዲስ መጣጥፍ ሊፈጥር ወይም ያለውን መጣጥፍ ሊቀይር ይችላል። አሁን ይፈትኑት! ዝም ብለው 'ይህን ገጽ ለማዘጋጀት' ከላይኛው ኅዳግ ተጭነው ከመስመሩ በታች ነገሮችን ይጨምሩ። ከዚያ 'ገጹን ለማቅረብ' ቢጫኑ ለውጦችዎ አሁኑኑ በመታየት ይሄዳሉ። አለዚያ ለውጡ ሳይላክ እሱን ለመመልከት ብቻ 'ቅድመ እይታ' መጫን ይችላሉ። ደግሞ ገጽ ሲያዘጋጁ 'ማጠቃለያ' በሚለው ሳጥን ውስጥ አጭር መግለጫ መጻፍ ጥሩ ምክር ነው።