Web Analytics Made Easy - Statcounter

See also ebooksgratis.com: no banners, no cookies, totally FREE.

CLASSICISTRANIERI HOME PAGE - YOUTUBE CHANNEL
Privacy Policy Cookie Policy Terms and Conditions
Wikipedia - እንግሊዝኛ

እንግሊዝኛ

ከWikipedia

እንግሊዝኛ መደበኛ የሆነባቸው አገሮች
እንግሊዝኛ መደበኛ የሆነባቸው አገሮች

እንግሊዝኛ የምዕራብ-ጀርመናዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ቋንቋ ነው። በዓለም ላይ በብዙ አገራት ውስጥ ይናገራል። የልደት ተናጋሪዎቹ ቁጥር 380 ሚሊዮን ያሕል ሲሆን በብዛት የምድር 3ኛ ቋንቋ ነው። ከዚህ በላይ እስከ 1 ቢሊዮን ሰዎች እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ይችሉታል።

እንግሊዝኛ በእንግሊዝ አገር ጀመረ። አንግል እና ሴያክስ የተባሉ ጀርመናዊ ጐሣዎች መጀመርያ የተናገሩት ጥንታዊ እንግሊዝኛ ይባላል። ነገር ግን ይህ እንደ ዛሬው እንግሊዝኛ በጣም አልመሰለም። በ441 አ.ም. ጀምረው እነዚህ ጐሣዎች ከጀርመን ወጥተው በብሪታኒያ ደሴት ሰፈሩ። ቋንቋቸውም የተጻፈበት "ሩን" በተባለው ጽሕፈት ነበር። በ7ኛ መቶ ዘመን ክርስትና ከተቀበሉ በኋላ ግን ቋንቋው በላቲን ፊደል ሊጻፍ ጀመረ።

ከ9ኛ መቶ ዘመን ጀምሮ ብዙ ሠራዊት ከዴንማርክና ከኖርዌ ወደ እንግሊዝ ስለ መጡ ተመሳሳይ ቋንቋ ስለነበራቸው ያን ጊዜ እንግሊዝኛ ከጥንታዊ ኖርስ አያሌ ቃሎች ተበደረ።

በ1058 ዓ.ም. ዊሊያም 1 "አሸናፊ" ከነሠራዊቱ እንግሊዝ አገርን ወርሮ ንጉስ ከሆነ በኋላ አዲስ መንግሥት ለማቆም መኳንንቶቹን ከፈረንሳይ ከሱ ጋራ አመጣ። የእንግሊዝ መንግሥት ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ለረጅም ጊዜ (300 አመቶች) እንግሊዝኛ ከትምህርት በቶች ተከለክሎ ቋንቋው ለጽሑፍ ሳይሆን እንደ መነጋገርያ ብቻ ስለ ቀረ በዚያን ጊዜ ብዙ ተለወጠ። እንግሊዝኛ በዚሁ ዘመን እጅግ ብዙ ቃላት ከፈረንሳይኛ ስለተበደረ በፍጹም ሌላ መልክ ይዞ አሁን መካከለኛ እንግሊዝኛ ይባላል። ቻውሰር አንድ ስመ ጥሩ የመካከለኛ እንግሊዝኛ ጸሐፊ ነበር።

በ15ኛ መቶ ዘመን "ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ" በሚባለው ለውጥ አናባቢዎቹ ተለውጠው የቋንቋው ድምጽ እንደገና ሌላ መልክ ያዘና ከዊሊያም ሼክስፒር ዘመን ጀምሮ "ዘመናዊ እንግሊዝኛ" ተብሏል።

እንግሊዝኛ ከሌሎቹ ልሣናት ለምሳሌ ከቻይንኛ፥ ከህንዲ፥ ከጃፓንኛ እና ከእስፓንኛ አንዳንድ አዲስ ቃላት ከመውሰድ አላቋረጥም። ከተለያዩ አገሮች የነበሩት ሊቃውንት እርስ በርስ ለመነጋገር የቻሉ የጋራ ካወቁት ከሮማይስጥና ከግሪክ የጥናቶቻቸው ቃሎች በመምረጥ ነበር። እነዚያ የተክኖሎጂ ቃሎች ደግሞ ወደ እንግሊዝኛ ገቡ፤ ለምሳሌ፣ photograph (ፎቶግራፍ) ከግሪክ photo- ፎቶ (ብርሀን) እና -graph ግራፍ (ሰዕል)፤ ወይም telephone (ተለፎን) ስልክ። ስለዚህ እንግሊዝኛ ከብዙ ቋንቋዎች ይሠራል።

በሌሎች ቋንቋዎች


aa - ab - af - ak - als - am - an - ang - ar - arc - as - ast - av - ay - az - ba - bar - bat_smg - bcl - be - be_x_old - bg - bh - bi - bm - bn - bo - bpy - br - bs - bug - bxr - ca - cbk_zam - cdo - ce - ceb - ch - cho - chr - chy - co - cr - crh - cs - csb - cu - cv - cy - da - de - diq - dsb - dv - dz - ee - el - eml - en - eo - es - et - eu - ext - fa - ff - fi - fiu_vro - fj - fo - fr - frp - fur - fy - ga - gan - gd - gl - glk - gn - got - gu - gv - ha - hak - haw - he - hi - hif - ho - hr - hsb - ht - hu - hy - hz - ia - id - ie - ig - ii - ik - ilo - io - is - it - iu - ja - jbo - jv - ka - kaa - kab - kg - ki - kj - kk - kl - km - kn - ko - kr - ks - ksh - ku - kv - kw - ky - la - lad - lb - lbe - lg - li - lij - lmo - ln - lo - lt - lv - map_bms - mdf - mg - mh - mi - mk - ml - mn - mo - mr - mt - mus - my - myv - mzn - na - nah - nap - nds - nds_nl - ne - new - ng - nl - nn - no - nov - nrm - nv - ny - oc - om - or - os - pa - pag - pam - pap - pdc - pi - pih - pl - pms - ps - pt - qu - quality - rm - rmy - rn - ro - roa_rup - roa_tara - ru - rw - sa - sah - sc - scn - sco - sd - se - sg - sh - si - simple - sk - sl - sm - sn - so - sr - srn - ss - st - stq - su - sv - sw - szl - ta - te - tet - tg - th - ti - tk - tl - tlh - tn - to - tpi - tr - ts - tt - tum - tw - ty - udm - ug - uk - ur - uz - ve - vec - vi - vls - vo - wa - war - wo - wuu - xal - xh - yi - yo - za - zea - zh - zh_classical - zh_min_nan - zh_yue - zu -